Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

ኢትዮ ቴሌኮም 24.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘ - 16.2 ቢሊዮን ብር ግብር እንዲሁም ሰባት ቢሊዮን ብር የትርፍ ድርሻ ለመንግሥት ፈሰስ እንዳደረገ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋ

Post by Dawi » 26 Jul 2019, 00:48

የፈረንጅ ላም ነው አለ መለስ? :P

ላም አለኝ በሰማይ ባይሆን ኖሮ!

አሁን ላም ለምን ይሸጣል ታዲያ?



ኢትዮ ቴሌኮም 24.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘ

24 July 2019
ቃለየሱስ በቀለ

በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ 204 ሚሊዮን ብር ገቢ አጥቷል

በአገሪቱ ብቸኛ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በ2011 በጀት ዓመት ያልተጣራ 24.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡

የኩባንያውን የአንድ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ማክሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከተደቀኑበት አደጋዎች ወጥቶ መልካም አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደቻለ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በአማካይ ከ40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ በማድረግ 36.3 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘ፣ ይህም የዕቅዱ 85 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት የሰባት በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ኩባንያው 16.2 ቢሊዮን ብር ግብር እንዲሁም ሰባት ቢሊዮን ብር የትርፍ ድርሻ ለመንግሥት ፈሰስ እንዳደረገ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡ ኩባንያው ለሦስት ዓመታት ያልተከፈለ 9.9 ቢሊዮን ብር ወይም 362 ሚሊዮን ዶላር ብድር ክፍያ መፈጸሙን እንደ ትልቅ ስኬት ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 43.6 ሚሊዮን የደረሰ መሆኑን፣ ከዚህ ውስጥ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች 41.92 ሚሊዮን፣ የዳታና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 22.3 ሚሊዮን፣ የመደበኛ ስልክ 1.2 ሚሊዮን እንደሆኑ ታውቋል፡፡ በአጠቃላይ የቴሌኮም ሥርፀት 44.5 በመቶ እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ 19 አዲስና 23 የተሻሻሉ የአገር ውስጥ ምርትና አገልግሎቶች የቀረቡ መሆናቸውን፣ አራት አዲስና 13 የተሻሻሉ ዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶች ለገበያ ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

የደንበኞችን የመግዛት አቅም በማገናዘብ የቴሌኮም አገልግሎትን አጠቃቀም ለማሻሻል ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚደርስ የታሪፍ ቅናሽ በሁሉም ምርትና አገልግሎቶች ላይ በመደረጉ 19 በመቶ የድምፅ ትራፊክ፣ 130 በመቶ የዳታ ትራፊክ ዕድገት መመዝገቡን ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት እየቀነሰ የመጣውን ዓለም አቀፍ ጥሪ አዝማሚያውን ለመቀልበስ፣ በበጀት ዓመት በተወሰዱ የቴክኒክና የቢዝነስ አማራጭ መፍትሔዎች የትራፊክ መጠን በ50 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ተገልጿል፡፡

ከውጭ በሚደረጉ ጥሪዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ማሻሻያ ስለተደረገበት ከፍተኛ የጥሪ ፍሰት ዕድገት እንደታየ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ገልጸዋል፡፡ እንደማሳያ ባለፈው ዓመት 288.5 ሚሊዮን ደቂቃዎች የውጭ ጥሪዎችን የተቀበለው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 433 ሚሊዮን ደቂቃዎች እንዳስተናገደ ተገልጿል፡፡ ከውጭ ጥሪዎች በወር ይገኝ የነበረው ገቢ ከ4.4 ሚሊዮን ዶላር ወደ 12 ሚሊዮን ዶላር እንዳደገ ተመልክቷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ ክፍል በማቋቋም ከውጭ አገሮችና ኩባንያዎች ጋር የነበረውን የሥራ ግንኙነት በማሻሻል የወጪ ገቢውን ማሳደግ እንደቻለ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር የነበረው የሥራ ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ2014 ከክፍያ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት ተቋርጦ በመቆየቱ፣ ኢትዮ ቴሌኮም በየወሩ አንድ ሚሊዮን ዶላር በሦስት ዓመት 36 ሚሊዮን ዶላር እንዳጣ ገልጸው፣ ችግሩን በውይይት በመፍታት ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ አገልግሎቱ እንዲቀጥል በመደረጉ በተዘዋዋሪ በሌሎች ኩባንያዎች አማካይነት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ይደረጉ የነበሩ ጥሪዎች፣ በቀጥታ በኢትዮ ቴሌኮም አማካይነት መስተናገድ እንደጀመሩ አስረድተዋል፡፡

የዱቤ አገልግሎት በመጀመሩ በበጀት ዓመቱ አራት ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ ከደንበኞች በስህተት የተቆረጠ 500 ሚሊዮን ብር የአገልግሎት ሒሳብ ተመላሽ መደረጉን፣ ከደንበኞች ያልተሰበሰበ 800 ሚሊዮን ብር ዕዳ ወደ 300 ሚሊዮን ብር እንዲቀነስ መደረጉን፣ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው መጠን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዕዳ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ወ/ሪት ፍሬሕይወት ኢትዮ ቴሌኮም ላስመዘገበው ውጤት የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ በተለይ የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በማኔጅመንቱ ላይ እምነት በመጣል ያቀረባቸውን ዕቅዶች በነፃነት እንዲያስፈጽም መፍቀዳቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ በመግለጽ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኩባንያው የገጠሙት ዋና ዋና ችግሮች የፋይበር ኦፕቲክስ መቆራረጥ፣ ስርቆትና የቴሌኮም ማጭበርበር እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በኔትወርክ መስመሮች ላይ 2,733 ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች መድረሳቸውን ይህም በአገልግሎት ጥራት ላይ መጓደል እንዳስከተለ ጠቁመዋል፡፡ የጥገና ሥራዎችን በአፋጣኝ ለማከናወን በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች እንከን እንደፈጠሩ ገልጸዋል፡፡

በስርቆትና በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች ላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ዕርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ገልጸው፣ ሕገወጥ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ለሕግ እየቀረቡ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ከአገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በየጊዜው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ በድርጅቱ ላይ ያደረሰው ኪሳራ ምን ያህል እንደሆነ በጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገባ ቀዳሚ ድርጅት በመሆኑና መንግሥት ከኩባንያው የሚያገኘውን ገቢ ለሌሎች መሠረተ ልማቶች ግንባታ የሚያውለው በመሆኑ፣ የኩባንያው ገቢ እንዲስተጓጎል እንደማይፈልግ አስረድተዋል፡፡

‹‹ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ መንግሥት ኢንተርኔት ማቋረጥ አይፈልግም፡፡ ነገር ግን ከገቢ በፊት ለአገርና ዜጎች ደኅንነት ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡ የአገር ደኅንነት አደጋ ላይ ሆኖ ስለገንዘብ ማውራት አንፈልግም፤›› ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ በፈተና ወቅትና በፀጥታ ችግር የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በመደረጉ 204 ሚሊዮን ብር ገቢ መታጣቱን አልሸሸጉም፡፡

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ በውጭ ኢትዮ ቴሌኮም በቀን 4.5 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን እንደተዘገበ፣ የአገር ውስጥ ሚዲያዎችም ይህንኑ ሲያስተጋቡ በመመልከታቸው ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኢትዮ ቴሌኮምም በላይ የሥራ እንቅስቃሴያቸው በኢንተርኔት ላይ የተመረኮዘ ኩባንያዎች ሥራቸውን በማስተጓጎል በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ፣ ለወደፊት የኢንተርኔት አገልግሎት ሳይቋረጥ ሁኔታዎችን መቆጣጠር የሚቻልባቸውን አማራጭ ዘዴዎች ላይ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ የቴሌኮም ዘርፍ ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት ማድረግን አስመልክቶ ኢትዮ ቴሌኮም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል የሚያስችለውን ዝግጅት፣ በተለይ በሰው ኃይል ሥልጠና ላይ ሰፊ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኩባንያውን በከፊል ወደ ግል ከማዛወር ሥራ ጋር በተያያዘም ቅድመ ዝግጅቶች በመካሄድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ በንብረት ምዝገባና የተንጠለጠሉ ሥራዎችን በመቋጨት ረገድ ትልልቅ ሥራዎች እንደተከናወኑ አስረድተዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም የሚመራበት የሦስት ዓመት መርሐ ግብር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች ቁጥር 15,646 የደረሰ መሆኑን፣ ሠራተኞች ተረጋግተው እንዲሠሩና የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የብድር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል፡፡

‹‹ደስተኛ ያልሆነ ሠራተኛ ይዘህ ደንበኛን ማስደሰት አስቸጋሪ ነው፤›› ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ ሠራተኛው ያለበትን የቤት ችግር መቅረፍ የሚያስችል ፕሮጀክት ከባንክ ጋር በመተባበር መቀረፁን ጠቁመዋል፡፡

125 ዓመታት ዕድሜ ያለውን ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዛወርና ሌሎች የውጭ የቴሌም ኩባንያዎች ገብተው እንዲሠሩ ለማድረግ መንግሥት ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/article/16258

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ኢትዮ ቴሌኮም 24.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘ - 16.2 ቢሊዮን ብር ግብር እንዲሁም ሰባት ቢሊዮን ብር የትርፍ ድርሻ ለመንግሥት ፈሰስ እንዳደረገ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸ

Post by Ethoash » 26 Jul 2019, 06:56

dawit

paying the worker with housing is my idea.. there r more idea i could give my two cent but first u go and answer my question about marriage u have to choice u choice one .. otherwise this great thread would be left without no reply or discussion..

Re;- በአክሊል ላግባ ወይስ በማዘጋጃ ላግባ መከሩኝ, I am Catholicism

viewtopic.php?f=2&t=190113

Post Reply