Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33783
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ (Cooperative Bank Of Oromia) አዲስ አበባ ለቡ ቅርንጫፍ ባለፈው እሁድ ለሊት ተዘረፈ

Post by Revelations » 06 Aug 2019, 22:03

ባንኩ 2,000,000 (2 ሚሊዮን) ገደማ መዘረፉ ተረጋገጠ!!

የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ (Cooperative Bank Of Oromia) አዲስ አበባ ለቡ ቅርንጫፍ ባለፈው እሁድ ለሊት ተዘርፎ ማደሩ ታዉቋል። የባንኩ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ እዉነት ተዘርፏል ወይ ተብለዉ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ትክክል ነዉ ባንካችን ተዘርፏል ጉዳዮን ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሄደ ነው ብለዋል። ዘራፊዎቹ እነማ ናቸዉ ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ የጥበቃ ሰራተኞ ከሌሎች ጋር ተመሳጥረዉ ነዉ ያሉ ሲሆን ጥበቃዎቹ በኤጀንሲ የመጡ ናቸው ስለሆነም የጥበቃ ሰራተኛ ያቀረበልን ኤጀንሲውም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል። እንደ አቶ በለጠ ገለፃ የተዘረፈው ገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም ያሉ ቢሆንም ከ1 ሚሊዮን 400,000 እስከ 1 ሚሊዮን 700,000 ብር ተዘርፏል የሚል ግምት ግን አለን ብለዋል። እገንዘብ ማስቀመጫዉ ተሰብሮ እንደተዘረፈ ታውቋል። ቅርንጫፉ ግን አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጠ ነው፣ የአገልግሎት መቋረጥም አላጋጠመም ሲሉ ተናግረዋል።





Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45811
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ (Cooperative Bank Of Oromia) አዲስ አበባ ለቡ ቅርንጫፍ ባለፈው እሁድ ለሊት ተዘረፈ

Post by Halafi Mengedi » 07 Aug 2019, 00:34

To whom do we have to hide and why want to hide, he was lecturing on camera and he gave interview with THM???

Revelations
Senior Member+
Posts: 33783
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ (Cooperative Bank Of Oromia) አዲስ አበባ ለቡ ቅርንጫፍ ባለፈው እሁድ ለሊት ተዘረፈ

Post by Revelations » 07 Aug 2019, 01:36

በጃፓን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዮኮሃማ በሚካሄደው የቲካድ 7 የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደዛው ለሚሄዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ልኡካቸው ኦገስት 27 የአቀባበል ሥነ -ሥርዓትና አጭር የውይይት መድረክ እያዘጋጁ ነው። ከቀናት በፊት እዛው ጃፓን በነበርኩበት ወቅት የሀገሪቱ ባለስልጣናትን ጠ/ሚር አብይ ይገኙ ይሆን ብዬ ጠይቄ "እርግጠኛ አይደለንም! ትንሽ ግርግር እና የፀጥታ መደፍረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ ላይገኙ የሚችሉበት እድል ሊኖር ይችላል። የግብዣ ደብዳቤ ግን በጃፓኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኩል ተልኳል" ብለውኝ ነበር።

Screenshot via Ethiopian Embassy in Tokyo


https://www.facebook.com/journalistelia ... =3&theater





Post Reply