Page 1 of 1

እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 19 Feb 2020, 02:24
by Horus
እሾሽላ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ታቃላችሁ ።

እንሾሽላ ከቀይ ስር የሚገኝ የሴቶች ቁንጅና ነገር ነው ፤ ሂና እንደ ሚባለው ።

በድሮ ዘመን አንዲት የጉራጌ ልጃገረድ (በተልይ ክስታኔ) ሰርጓ እንደ አንድ ወር ሲቀረው ጥፍሯ ይቆረጥና ወይ ለወር፣ ወይ ለ3 ሳምንት "የጥፍር" ይጨፈር ነበር ።

ከዚያም ሰርጓ 3 ወይ 4 ቀን ሲቀረው አሁን የምታዩት "እንሾሽላ" ይታሰርላት ነበር ። እንሾሽላ ያግድልችኮይ ማለት እንሾሽላ ሲታሰርልሽ ማለት ነው ።

ዛሬ ይህ ባህል በጭፈራና ፌስታ ደረጃ ለሴቷም ለወንዱም ሆነ እንጂ ድሮ ይህ የሴቶች ወግ ብቻ ነበር። ለወንዱ የወሬ ነሀ ጎሽ፣ ወይም የወቅቱ፣ የግዜው፣ የወረቱ ሰው ነህ እየተባለ በሰርጉ ቀን ይዘፈንለት ነበር።

ሴቷ ግን ወላጅ ዘመድ ተለይታ ላንዴም ለሁሌም ሌላ ዘር፣ ሌላ ቤት ስለምትሆን እንሾሽላ እጅግ የሚያሳዝን፣ ሆድ የሚያባባ የእናቶች፣ ያባቶች፣ ያያቶች፣ ያክስቶች፣ የዘመድ አዝማድ መሰናበቻ ትልቅ፣ ትልቅ ምሽት ነበር ።

በነጠላ ስር የተሸፈኑት ሙሽራና ሚዜዎቿ በእምባ ይራጩ ነበር፣ የነሱም ጓደኘት መለያያ ወቅት ስለሆነ ። የሴት ጥብቅ ጓደኞች (ቤስት ፍሬንድስ) ዬጎስቴ ይባባላሉ !! ሞክሼ እንደ ማለት ነው !!

የዘፈኑ ቃላት የሚሉት፣ እንሾሽላ ሲታሰርልሽ የእክሌ ልጅ ነኝ በይ እየተባለ ዘር ማንዘሯ በስም ይጠራል ። ግጥሙን ዜማውን ሁሉ የሚያወዱት ራሳቸው እናቶች አባቶች አያቶች ናቸው ።

ዛሬ ይህ ወግ ለወንዶችም እየተደረገ ነው ።

የዎሬ ነሽ ማለት ይህ ቀንሽ ነው፣ ይህ ወራትሽ ነው ፣ ይህ ያንቺ ወረት ነው ማለት ነው !!

ለወንዱም ያው ይህ ያንተ ሰአት ነው ማለት ነው !!!


Re: እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 19 Feb 2020, 03:11
by Horus

Re: እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 19 Feb 2020, 03:27
by Horus
ይህ ከዚህ በታች የምትሰሙት የዎሬ ነሀ ጎሽ ወንዱ ሙሽራ ወደ ሙሽራዋ ቤት ለመሄድ ፈረሰኛ ሚዜና አጃቢዎቹን ይዞ ሲወጣ " በል እለፈ እለፈ ጉወ ትመስሉ ዎፈ" በል ሂድ፣ በል ሂድ ተውበህ ወፍ ትመስላለህ" እየተባለ የወሬ ነህ፣ የወረት ነህ ፣ የግዜው ነህ እየተባለ ሲዘፍኑለት ፤ የወለኔ ጉራጌዎች፣ የናቴ ዘሮች !!!


Re: እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 19 Feb 2020, 04:41
by Horus
የተምቢ ሙሽራ፣ የተምቢ ሙዜ፣ ዬምጣቢ ሙሽሪ፣ ዬምጣቢ ሚዞቺ ፣ ሙሽሮች እንኳን መጣችሁ !! ዋና ሚዜ የታለ ሻኛው፣ የታለ ጭኮው? !!!


Re: እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 19 Feb 2020, 05:55
by Wedi
እንሶስላ ነው የሚባል በአማራ አካባቢ ደግሞ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶር ሂሩት ካሳዉ ስለ እንሶስላ የሰጠችውን ማብራርያ ከዚህ ላይ ተመልከት!!



Re: እሾሽላ፣ አንዱን የጉራጌ ሰርግ ባህል ላስተዋውቃችሁ

Posted: 20 Feb 2020, 03:58
by Horus