Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ብልፅግናን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች የፖለቲካ አቋማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ!

Post by Ejersa » 23 Sep 2020, 12:34

ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ 11 የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለ በ10 ነጥብ የፖለቲካ አቋማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የተፈራረሙት ፓርቲዎች ብልፅግና ፓርቲ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ የመላው አማራ ህዝብ ፓርቲ፣ ነፀብራቅ አማራ ድርጅት፣ የኦሮሞ ነፃነት ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ፣ የአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ እና የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ናቸው። ፓርቲዎቹ ከስምምነት ላይ ደርሰው
የተፈራረሙባቸው ነጥቦች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉን አካታች የሆነ ቀጣይ ሀገራዊ ውይይትና ድርድር ማካሄድ፤
2. ጥርጣሬ፣ መከፋፈል፣ እርስ በርስ መቃረን፣ አንዱ የሌላውን ስም ከማጥፋት እንዲሁም ሕዝብ ለሕዝብ ከሚያጋጩና ከሚያቃርኑ ድርጊቶች መቆጠብ፣
3. ሀገራዊ የህዝብ ቆጠራ ተአማኒነትና ተቀባይነት ባለው አሠራር በማካሄድ የሁሉም የሀገሪቱ ብሔር ብሐረሰቦች የሕዝብ ብዛት በአግባቡ ተቆጥሮ እንዲታወቅ ማድረግ፤ በትክክል እንዲቆጠር፣ የከዚህ በፊት ግድፈቶች የሚያርምና የማይደገምበት መሆኑን ማረጋገጥ፤
4. በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መገንባት፣ የግልና የቡድን መብቶችን ማስከበርና በየጊዜውና በየደረጃው ነጻና ፍትሐዊ ምርጫን ማካሄድ፣
5. በኢትዮጵያ የታሪክ አቀራረብ የታሪክ አንጓዎችን ተከትሎ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በተወጣጡ የታሪክ ምሁራን የሀገሪቱን ህዝቦች ግንኙነትና ታሪክ ጥናት እንዲካሄድ፤ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም እንዲቋቋም፣
6. በኦሮሞና አማራ ክልሎች የሚኖሩ የሁሉም ህዝቦች አባላት ደህንነትና መብቶች እንዲከበሩ፤
7. በሀገራችን የሁሉም አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ፣ ህግና ፍትህ ማስፈን፤ ከየቦታው ያለአግባብ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸውና ኑሯቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤
8. ሀገሪቱ የምትተዳረርበት ሕገ መንግሥት ሁሉን አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲሻሻል ማድረግ
9. በሀገሪቱ ዘላቂና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ልማት ማጎልበት፤ የህዝቦቻችንን ፍትሀዊ የኢኮኖሚና የሀብት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
10. የተለያዩ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ዝግጅቶችን በጋራ ማዘጋጀት ናቸው።

ፓርቲዎቹ ለ10 ወራት ያህል በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ ቆይተው በ10 ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል።

የውይይታቸው መነሻ ባለፈው ዓመት በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ግጭቶች መከሰታቸውና ከዚህ ጀርባ የፖለቲካ ተዋንያን አሉ በሚል ግንዛቤ ሁኔታውን ለማርገብ መሆኑ ተገልጿል።

ከሁለቱም አካላት ገለልተኛ ሰዎች ተመርጠው ሲያወያዩ መቆየታቸውም ተገልጿል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ውይይት ባካሄዱበት የጋራ የፖለቲካ አቋመማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ በሸራተን አዲስ ተፈራርመዋል።

የፓርቲዎቹን ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ዓመት ሕዳር ላይ ማስጀመራቸው ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ፦ EBC

gagi
Member
Posts: 627
Joined: 16 Jun 2013, 16:34

Re: ብልፅግናን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች የፖለቲካ አቋማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ!

Post by gagi » 23 Sep 2020, 15:48

This is a significant step in the current political dynamics. A consensus among the political parties working with the two population groups is certainly a guarantee for Ethiopia's stability.

Such collaboration and understanding are also the best measures to prevent or defeat any sabotage by the TPLF traitors!

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11712
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ብልፅግናን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች የፖለቲካ አቋማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ!

Post by Noble Amhara » 23 Sep 2020, 16:06

Bilitgna is racist it promotes Nestanet/Bilsumma for Oromos and Slavery Delusional cancer non existing Ethiopianwit for real amharas Governed by former Weyane anti Fano anti human anti Amhara ADP cursed bantugojames subjects who deny the killing and genocide go amharas this Bilitgna is a part of the problem Bilitgna is racist Bilitgna is tribal Bilitgna is corrupt and only shows oromo dominance Bilitgna does not give amharas human rights Bilitgna makes amharas humanless Bilitgna treats amharas like aliens Bilitgna hires Weyane cadres that sold there soul to the devil Tigray to join EPRDF now they are PP there is no real Amhara in Bilitgna or Arat Kilo if Abiy wants to improve his relation with Amhara he should k!ll himself dictator

Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ብልፅግናን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች የፖለቲካ አቋማቸውን በያዘ ሰነድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ!

Post by Ejersa » 23 Sep 2020, 16:48

TPLF jealousy! TPLF has gone from power forever :lol: :lol: :lol: :lol:
Noble Amhara wrote:
23 Sep 2020, 16:06

Post Reply