Page 1 of 1

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መግታት የሚቻለው መንገድ በመዝጋት ሳይሆን አካውንትን በመዝጋት፣ ብሩን በመውረስ ነው!

Posted: 24 Sep 2020, 11:44
by Ejersa
የኢትዮጵያ መንግስት ተነሳሽነቱና ቁርጠኝነቱ ካለው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መግታት በጣም ቀላል ነው። ለምሳሌ ብዛት ያላቸው የኢትዮጵያ ዜጎች በሚኖሩባቸው እንደ አሜሪካ፥ ካናዳ፥ እንግሊዝ፥ ጣሊያን፥ ኖርዌይ፥ ጀርመን፥ አውስትራሊያ፥ ደቡብ አፍሪካ፥ ሳውዲ አረቢያ፥ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት፥.... ወዘተ የተወሰነ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ እንዲላክ በማድረግ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሰማሩትን አካላት አድራሻና የሚጠቀሙበትን የባንክ አካውንት በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። በተመሣሣይ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ገንዘብ በመላክ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎችን መለየት ይቻላል።

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መግታት የሚቻለው መንገድ በመዝጋት ሳይሆን የሌቦቹን የባንክ አካውንት በመዝጋት ነው። በዚህ መሠረት በጎረቤት ሀገራት እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየርመንገድ የበረራ አስተናጋጆች አማካኝነት የሚዘዋወረው ገንዘብ ከተወረሰና በዚህ ተግባር የተሰማሩት ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ፤

አንደኛ፦ ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው ገንዘብ በህጋዊ መንገድ በባንኮች በኩል ይሆናል።

ሁለተኛ፦ ወደ ውጪ የሚላከው ገንዘብ በህጋዊ መንገድ በባንኮች በኩል ይሆናል።

ሦስተኛ፦ በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ገንዘብና የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ይቀንሳል

አራተኛ፦ በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ የተሻለ የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ይገኛል።

አምስተኛ፦ የውጪ ምንዛሬ በብሔራዊ ባንክ ተመን መሠረት ሲሆን ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ይቀንሳል።

ስድስተኛ፦ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴና የኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

ሰባተኛ፦ እንደ ህወሓት ያሉ አሸባሪ ቡድኖች የሚያደርጉት አፍራሽ እንቅስቃሴ ይቀንሳል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦