Page 1 of 1

መስቀል ና አረፋ፡ እጅግ ታላቁ የጉራጌ ቃል ኪዳን ካልቸር

Posted: 25 Sep 2020, 03:28
by Horus
ባሁን ወቅት የተለያዩት የጉራጌ ማህበረሰብ አባላት የኬርታ፣ የዱዓ እና የፈቸት ባህሎች በአንድ ቀና በአንድ አሳብ ለማክበር ፕላን እየተደረገ ነው።

ይህ ምን ማለት ነውተ

ድሮ ድሮ በአዲስ አመት ቀን የባህል እምነት መሪዎች ያለፈውን አመት ገምግመው ላዲሱ አመት ተስፋና ቃል የሚገባበት ቀን ነበር ። ዛሬም የሚሆነው ያው ነው ። ልክ እንደ ድሮ ቃል ሚናገሩ ሚመርቁ ፣ ሚተነብዮ አበው እና ልሂቃን አሉ ። በአንድ ቃል በመስቀል ሰው ሁሉ ልጅ ሆነ አዋቂ ያለፈውን አመት ስኬት የሚያመሰግበት ቀን ነው። የሰጠ የሚመረቅበት የባርኮት ቀን ነው ። ለሚቀጥለው አመት ቃል ኪዳን የሚገባበት ቀን ነው። ጥል ያበቃል፣ መራራቅ ያበቃል ፣ በአንድ ቃል መስቀልም ሆነ አረፋ የቃል ኪዳን ማስረገጫ ቀን ነው።





Re: መስቀል ና አረፋ፡ እጅግ ታላቁ የጉራጌ ቃል ኪዳን ካልቸር

Posted: 25 Sep 2020, 03:39
by Horus