Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Educator
Member
Posts: 2022
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

He releases criminals for holidays and kidnaps journalists on new year. Satan Mamo Killo

Post by Educator » 11 Sep 2022, 17:01

ዛሬ በዘመን መለወጫ ቀን በጠዋት ስልኬ ጮኸ ፣አነሳሁ የብርቱው ወንድሜ የአሳዬ ደርቤ ባለቤት ነች ።

ድሞጿ ይንቀጠቀጣል፣እንባዋ ይታገላታል፣ደሞ እኔን ለማናገር ትሰቃያለች!😑 "ምን ሆንሽ?" አልኳት ልቤ የጠረጠረውን በልቤ ይዤ። "አሳየን ወሰዱት፣ከልጆቹ ጋር በተቀመጠበት ፣ልጆቼ እያለቀሱ" አለችና ለቅሶዋ አሸነፋት!

ምሬት ሰውነቴን ሲቆጣጠረው ተሰማኝ፣ለማን በመቆሙ እንዲህ እንደሚደረግ ገባኝ፣ መድሃኒቱ ትከሻን ማበርታት እንደሆነ ተሰማኝ። "በቃ ዝም በይ ማልቀስ በቃን ! ይታሰር ምን ይሆናል" አልኳት። "እሱን አውቃለሁ ልጆቼ ፊት ሲወስዱት የሆኑትን ብታይ እኮ" አለች አሁንም እንዛዋ እያሸነፋት።"የእኛ ልጆች አለቀሱ ብለን እናወራለን የሚገደሉ ህጻናትም አሉ፣አሳዬ የታሰረው ለሚገደሉት ህጻናት ነው ፤ ለእሱ ልጆች አንች አለሽ በርታ በይ ምንም አይሆንም" አልኳት ስሜቷ ያላመመኝ፣ጭንቀቷ ያልከበደኝ መስዬ!!!!!

ሲጠቃለል አሳዬ ደርቤ በአል ቀን ፣ ከልጆቹ ጉያ ተነጥቆ፣ ሚስቱ እያነባች እስር ቤት ተወርውሯል - ወደ ዝነኛው ሜክሲኮ ማጎሪያ¡¡¡
ይሄው ነው!!!!

Meskerem Abera