Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

የሲዖል የበኩር ልጅ

Post by Assegid S. » 12 Sep 2022, 12:33

እውነት ለመናገር፦ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚንስትር በየትኛውም አቅጣጫ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚናገሩትንም ሆነ እንዲነገርላቸው የሚፈልጉትን ማናቸውንም ነገር ለማመን በጣም እቸገራለሁ ብቻ ሳይሆን ፈፅሞ ለማመን አልችልም!። ባለቤቱን (ቀላቢውን) ካላመኑ ደግሞ ውሻውን (ተቀላቢውን) ማመን ያስነክሳል።

ይሁንና ግን፦ "ህወሃት አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ልጆች በጥይት እንዲመቱ አዘዘ" የሚለውን ዜና በተመለከት፥ ህወሃት የራሱን ልጆች ከኃላ አይመታም ወይንም ደግሞ አያስመታም የሚል ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም። ይህ የሲዖል የበኩር ልጅ ከዚህም በላይ ያደርጋል ... ያስደርጋል። ለዚህም ... በበሉበት የሚጮዂት ውሾች ሳይሆኑ የገዛ ራሴ ዓይንና ጆሮዎች እማኞቼ ናቸው።

የሆኖ ሆኖ ... ይህን ዜና ከሰማሁ ቀናቶች የተቆጠሩ ቢሆንም፥ ዛሬ ER ላይ ከረምረም ያሉትን threads በወፍ በረር ስቃኝ ኣንድ አሳዛኝ ምስል ተመለከትኩና ይህን ጉዳይ በድጋሚ ለማንሳት ፈለኩ።

እነዚህ ምስኪን ሴት እህቶቻችን ሳይወዱ በግድ ከቤታቸው ታፍሰው ተወስደው በማያውቁትና ሞያቸው ባልሆነው (ልምድ በሌላቸው) ጦርነት መሃል በግዳጅ ገበተው ሰለባ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ለዚህም ምስክሩ ደግሞ አንደኛዋ እህት ቆስላ የነበረው ከጀርባዋ መሆኑ ... ኣንድም በህወሃት ጥይት ከጀርባ፥ አሊያም ያለውዴታዋና ልምዷ ከገባችበት ጦርነት በመሸሽ ላይ ሳለች ለመመታቷ እንደ ጠቋሚነት ሊቀርብ ይችላል። ስለዚህ አሳዛኝ ፎቶ ብዙ ማለት ብፈልግም ለጊዜው ባለመቻሌ ... ጥቂት ብቻ እንደሚከተለው ብያለሁ:



ድፍትትት … ብላ ባያት
ወገኔ የምላት
ያለ ፈቃድ ልምዷ … ለ-አረር የማገዷት

ተጉዞ ተጉዞ … ነፍሷ እጅግ ርቆ
ባልችል ልመልሳት … በእንባ፣ በለቅሶ

ስንቅ ቢሆናት ብዬ … ለተራበ ኣንጀቷ
ልቋጥር ብነሳ
የፊደል አገልግል … ስንኝ-ቢጤ ምሳ

ውስጤ ሓሳብ አርግዞ … ደርሶ ይጨነግፋል
ለካስ የሀዘን ዱላ እንዲህ ብርቱ ኖሯል
ልብን ብቻ ሳይሆን ጣትንም ይሰብራል?