Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30991
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በአንድ እራስ ሁለት ምላስ፣ በአንድ አገር ሁለት የጦር ድርጅት ሊኖር አይችልም! የትግሬ ድርድር ተረት!!

Post by Horus » 12 Sep 2022, 13:32

እኔ ሆረስ ቃላት መሰንጠቅ አይመቸኝም! እርግጥ የትግሬ ችግር የፖለቲካ ችግር ስለሆነ መፍትሄው ፖለቲካ ነው ። ነገር ግን ትህነግ የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን የጦር ድርጅት ነው ። ትህነግ እንደ ጦር ድርጅት ብልጽኛ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ፈጽሞ የፖለቲካ ድርድር ሊያደርጉ አይችሉም።

ቲዲኤፍ ፈርሶ ሲቪል የትግሬ ፖለቲካ ፓርቲ ከተፈጠረ ብቻ ነው የትግሬ ችግር የሚፈታው ። ያ ደሞ እንዲህ ባጭር ግዜ አይሆንም ። የኢትዮጵያ ጦር ትግሬን በኮማንድ ፖስት ቢገዛ እንኳን ትህነግ የጎሬላ ጦርነት ማድረጉ አይቀሬ ነው ።

ትህነግ አሁን እያደረገ ያለው የትግሬ ጦርነት ወደ አለም አቀፍ ውዝግብ ሄዶ ልክ እንደ አንድ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመገዳደርና አለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ነው ።

ትግሬ መንገንጠል ነው የሚፈልገው! ችግሩ አለም አቀፍ እውቅና ማጣቱ ነው ። አሁን ያለው የትህነግ ስራ ሁሉ ለዚያ እስትራተጂክ ግብ መሳካት የሚደረግ ዘርፈ ብዙ ትግል ነው ።

ትህነግ የትግሬ ብልጽግና ፓርቲ የመሆን ፍላጎት በውኑ አይደለም በህልሙም የለም!!! ይህን እነአቢይ ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ! መልሱ ያለው የኢትዮጵያ ጦር በሚያደርገው ንቅናቄ ነው ።


ሆረስ ሃይለ ብርሃን
Last edited by Horus on 12 Sep 2022, 13:54, edited 1 time in total.


Post Reply