Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33333
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Images Of:የደጀኑ ህዝብ ደጀንነት:-የሰሜን ወሎ ዞን የጉባ ላፍቶ ወረዳ ህዝብ ለጥምር ጦሩ ስንቅ ሊያቀብል ዛሬ እንዲህ ሲተም ውሏል(WOW,IMPRESSIVE)!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 13 Sep 2022, 10:12



https://scontent-atl3-1.xx.fbcdn.net/v/ ... e=6325805B[/image]




Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

·
የደጀኑ ህዝብ ደጀንነት‼️
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ወሎ ዞን የጉባ ላፍቶ ወረዳ ህዝብ ለጥምር ጦሩ ስንቅ ሊያቀብል ዛሬ እንዲህ ሲተም ውሏል።
እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተካተተበት ሰልፈኛ ስንቁን ሸክፎ ለአገር ክብር እየተዋደቀ ላለው ሰራዊት ስንቅ ለማቀበል ሲጣደፍ በስፍራው የሚገኙት የኢፕድ ዘጋቢዎች ተመልክተዋል።
የጉባ ላፍቶ ወረዳ ነዋሪዎች እንጀራ፣ ዳቦ፣ በግ፣ ፍየል ሰንጋና ሌላም ሌላም ነገሮችን ይዘው ሲያቀኑ በኩራት ነው።
በግንባር ተገኝተው ድጋፍ ካደረጉ ዜጎች መካከል ሃሳባቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች የሰጡት የጉባላፍቶ ወረዳ ነዋሪዎች፤ "ህይወቱን ለሚሠዋ ሠራዊት ከዚህም በላይ ድጋፍ ልናደርግ አንሻለን" ሲሉ ነበር የተናገሩት።
ከሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ውድበኝ ቀበሌ የመጡት አርሶአደር ወይዘሮ የልፍኝ ደምሴ፤ ወራሪውን ቡድን ለመመከት በግባር ለሚገኘው ሠራዊት የስንቅ ድጋፍ በማድረግ አጋርታቸውን መግለጽ በመቻላቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
የድፎ ዳቦ ጋግረው ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር ያደረሱት ሌላኛዋ እናት ደግሞ ከጉባላፍቶ ወረዳ ጌሾበር ቀበሌ የመጡት ወይዘሮ ፋንታዬ አሊ ናቸው።
እርሳቸወም ህይወቱን መስዋዕት በማድረግ ለአገራችን ሠላም ለሚዋደቀው ጦር በቀጣይ ከዚህም በላይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
በተመሳሳይ ሌሎችም ይሄንኑ ነው የደገሙልን፤ ለአገር ክብር ለሚዋደቀው ሰራዊት ስንቅ ማቀበል የእኛ የደጀኑ ህዝብ ግዴታ ስለሆነ ይሄንን በማድረጋችን ኩራትና ክብር ይስማናል ብለዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio