Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 14:09

አንድ፣
አሁን ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ የማስተዋል ፖለቲካ ትፈልጋለች ። ፊውዳሊዝም ሞክረን አልሰራም፤ ሶሺያሊዝም ሞክረን አልሰራም፣ ጎሳኢዝም (ኤትኖክራሲ የትግሬና ወረሞ) ሞክረን አልሰራም ። አሁን የኢትዮጵያ ምሁራን ከዳር እስከ ዳር ተነስተው አዲስ የሚቀጥለውን የፖለቲካ ህሳቤ ላይ ግዙፍ ምርምር፣ ክርክርና ውይይት መጀመር አለባቸው ። ለምን ቢባል?

ሁለት፣
የሕዝቡ አገር አቀፍ ንቅናቄ የፖለቲካ ኢሊቱን (ልሂቁን) አልፎ ሄዶ አዲስ አገር የማደራጃ ንድፈ ሃሳብና ሞዴል ባስቸኳ እየጠየቀ ነው ። ባቢይ አህመድ የሚመራው የወረሞ ተረኛ አገዛዝ ገና ሃ ብሎ ሲጀመር አንስቶ ሽባ ሆኖ የተወለደ፣ በሽተኛና በጭለማ ውስጥ ለ5 አመት ሲመላለስ ከርሞ አሁን በሁሉም መስክ በሚባል ደረጃ መስራት አቅቶት የቆመ ያላዋቂዎች መንገድ ነው። የትግሬ ዘረኛ ይህን መንገድ ለ27 አመት ተጉዞ ምን ላይ እንደ ቆመ አለም ሁሉ መስክሯል ።

ሶስት፣
የዊዝደም ፖለቲካ ወይም የስነ አስተውሎት ፖለቲካ መጀመሪያው አንድ ሰው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ወይም ፕሬዚዳንት ለመሆን 60 አመት ወይም ከ60 አመት በላይ እድሜ ያለው ሰው ብቻ መሆን አለበት ።

አራት፣
በአለም ላይ ላለፉት 2 ሺ ወይም 3 ሺ አመታት የሰው ልጅ ያካበታቸው የፖለቲካ ዊዝደሞች፣ አስተውሎቶች፣ ጥብቦች አሉ ። ይህ የጥበብ ጥያቄ ለአንድ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትክክለኛ የአስተዳደር አይነት የቱ ነው የሚለው መመለስ ሲሆን ለዚህ ብቸኛ ጥያቄ የጥበበኛ መልስ የሚሰጥ ስነ መንግስት ባስቸኳይ ለውውይይት መቅረብ አለበት ።

አምስት፣
ከላይ እንዳልኩት መጀምሪያ የበላይ መሪዎች እድሜ ነው ። ቀጥሎ የዚያ መሪ (መሪዎች) ዊዝደም ነው ። የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ መወገድ አለበት ።

ስድስት፣
የፖለቲካ ፓርቲ ያላዋቂና ሌብነት፣ ሙሰኝነት መፍለቂያ ረግረግ ሰልሆነ የፓርቲ አደረጃጀት ሲስተም ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አለበት ።

ሰባተኛ፣
ልክ እንደ ፓርቲ ሃሳብ ፌዴራሊዝም የተባለው አሰልቺ፣ ምን እንደ ሆነ የማይታወቅ ባዕድ ሃሳብ ተሰርዞ ሌላ ከህዝባችን ባህልና ታሪክ የፈለቀ ያስተዳደር ስርዓት ለውይይት መቅረብ አለበት ።

በዚህ መልክ በመከላከያ፣ ፖሊስ፣ ጸጥታ፣ ኢኮኖሚ፣ ሌላም ሌላም ላይ አሁን ተብለው ተብለው የጃጁት የማይሰሩ የቆሸሹ ሃሳቦችና ሲስተሞች ተለቅመው መዘረዝና በመሰረቱ አስተዋይ በሆኑ በዊዝደም ጽንሰ ሃሳቦች መተካት አለባቸው ።

ስምንተኛ፣
አንድ ሕዝብ ያለ ሶሺያልና ፖለቲካ ስርዓት ብዙ ዘመን መኖር እንደ ማይችል ሁሉ አንድ ሕዝብ በተሳሳተ ስርዓት ውስጥ ብዙ ዘመን መኖር አይችልም፤ ይወድማል፣ ይበተናል ፣ እንደ ሕዝብ እንደ አገር ይጠፋል ። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ይህን መሰል አደጋ ላይ ደርሳለች ።

ሆረስ ኃይለ ብርሃን

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 14:39

አዲሱ የፒፒ አጀንዳ!

አሜሪካ አቢይን አይፈልግም!

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 14:53

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 15:06

ስለ አቢይ አህመድ አላዋቂ ስብስብ ቡድን ጂልነት ይህን ድንቅ ትችት ስሙ!!

Tiago
Member
Posts: 2054
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Tiago » 23 Jun 2023, 15:27

ሰባተኛ፣
ልክ እንደ ፓርቲ ሃሳብ ፌዴራሊዝም የተባለው አሰልቺ፣ ምን እንደ ሆነ የማይታወቅ ባዕድ ሃሳብ ተሰርዞ ሌላ ከህዝባችን ባህልና ታሪክ የፈለቀ ያስተዳደር ስርዓት ለውይይት መቅረብ አለበት ።

Federalism is not bad for Ethiopia as long as it is not hijacked and mixed with narrow ethnic politics.
ethnocentric politics shrouded in the name of defending ethnic groups from fictional exploitation must be seen not different from Nazism or racism and must be banned altogether.

እብዱ አብይ አሰብን ለማስመለስ የጋላና የአጋሜ ጀሌ ይዞ ይሞክረው

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 15:37

Tiago wrote:
23 Jun 2023, 15:27

ቲያጎ፣
ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ የሆነ የራሷ ቃል አላት፣ እሱም ራስ ገዝነት (ራስ ገዥነት) ይባላል። ይህ ቃል በሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አለ ። የፌደረ ስረ ቃል መተማመን ማለት ነው እንጂ ራስ ገዥ ፣ አጉራ ጠነ፣ እራሱ የጠና ማለት አይደለም ። ያስተዳደር ስልጣን (ኃይል) ከተማ ከተከማቹ ሌቦችና ፓርቲዎች ተቀምቶ ወደ እራሱ ሕዝቡ የሚወርደው 'ራስ ገዥ' በሚለው ጽንስ ብቻ ነው ። ለምሳሌ አቢይ አህመድ የተባለው አላዋቂ በምን ሎጂክ ነው ራያ እንዴት እንደ ሚገዛ የሚወስነው? ይህ መሰል ቆሻሻ ሃሳብ ነው ከፖለቲካ ባህላችን ማጽዳት ያለብን ።

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by sarcasm » 23 Jun 2023, 15:57

Horus wrote:
23 Jun 2023, 14:09
አንድ፣

ሰባተኛ፣
ልክ እንደ ፓርቲ ሃሳብ ፌዴራሊዝም የተባለው አሰልቺ፣ ምን እንደ ሆነ የማይታወቅ ባዕድ ሃሳብ ተሰርዞ ሌላ ከህዝባችን ባህልና ታሪክ የፈለቀ ያስተዳደር ስርዓት ለውይይት መቅረብ አለበት ።

Federalism a.k.a Neguse Negest system is an organic millennia old Tigrayan system & a gift to Ethiopian peoples nations and nationalities.

The Neguse Negest system is an organic federalist system devised by Ancient Tigrayans in Axum. The core foundations of the system are autonomy, self-rule and respect for differences. Hence, the Abyssinia / Ethiopian Empire has always been a federalist arrangement.

The Neguse Negest system is a federalist system where the Neguses have autonomy on their territories and pay taxes to the Neguse Negest (federal government). The Neguse Negest looks after common defense and international relations. Actually, it looks like it was HSI who ended the federalist system when he fired the Neguses but still kept the Neguse Negest title. He introduced a centralized state system into a country that has always been a federalist structure. Mengistu continued the madness of unitary state which resulted in Eritrea's independence.

The Isaias, Abiy & Amhara Elite / fake 'Ethiopianist' alliance have plunged the country into another bloody war after 30 years in order to re-install a centralized / unitary state system and end the existing Constitutional Federalism. Tigray has single-handedly defeated the Alliance and forced PM Abiy & his PP to commit to keep Constitutional Federalism.

On the current ethnic killing, it is the politicians that are using ethnicity for political killings in Ethiopia. The politicians in previous administrations were not determined to cleanse areas from different ethnicity by killing and displacing the other ethnicity. Now politicians in some Oromia region areas are killing Amharas and the Amhara politicians in some Amhara region areas are killing Oromos. I don't think people forget the placement & murders by stoning of Tigrayans in church in Gondar few years ago. Amhara region's ethnic cleaning of Tigrayans in Western Tigray is now internationally recognized 21st century crime.

"የእትዮጵያ ትልቁ ችግር ethnic federalism አይደለም።" ዶ/ር መሳይ ከበደ

Unitarist political elite started accepting the war to dismantle constitutional multinational federalism and install unitary government system has been lost. TDF saved self rule for Tigrayans and the rest of Ethiopia. Prosperity Party has accepted constitutional multinational federalism.

Unitarist political elite have started accepting that constitutional multinational federalism has won in the battle front and will always win in the ballots. Things are moving the right direction.

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 23 Jun 2023, 16:42

ሳርካስም፣
አሁንኮ እስከ ሚሰለች የምትደጋግመው ላለፉት 60 አመታት ጉንጫችንን ያለፉት አሰልቺ ድግግሞሽ ነው። የምትለው ፌዴረ እኮ ነው የዘር እልቂት ጄኖሳይዳዊ ሲስተም የሆነው ። መሳይ ከበደ የደቡን ኤትኖ ፌደረ ነው። የሱም ሃሳብ ያረጀ ነው።

ንጉስና ንጉሰ ነገሰ ምንም ከራስ ገዝነት ጋር የሚገናኝ አይደለም ። ፊውዳል ሲስተም ነው ። በፊውዳል ሲስተም አንድ ጉልበተኛ እግዚአብሄር ስለሾመኝ ሕዝቡም መሬቱም የኔ ብሎ ከዘር ዘር ይገዛል ። ሕዝቦቹ ሰርፍ ወይም ባሪያ ይባላሉ ።

በኋላ ሌላ የትግሬን ጉልበተኛ የሚበልጥ ጉልቤ የመጣና ንጉሱ ከባሪያዎቹ ከዘረፈው ግብር እንዲቆረጥለት ያስገድዳል ። ንጉሱ የንጉሰ ነገስቱ ግብር ሰብሳቢ ይሆናል ! ይህን መሰል ፌውዳል ሰፍደምን ነው አንተ ፌደራሊዝም የምትለው ። እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ !! አው ምኒልክ ከአባ ጅፋር ስልጣን አልቀማውም ግ ን አባ ጅፋር ባሪያ ነጋዴ ነበር እንጂ የጂማ ሕዝብ እራሱን የሚገዛ ነጻ ሕዝብ አልነበረም ። ዛሬም አይደለም !! ፒፒ የሚገዛው ዘመናዊ ሰርፍ ነው!

የትግሬን እንተወው !

Abere
Senior Member
Posts: 11143
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Abere » 23 Jun 2023, 16:59

አዎን የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ethnic federalism ነው። ይህን ሀቅ ለማወቅ ጥልቅ ትምህርት እና ዕውቀት የሚፈልግ አይደለም። ለአለፉት 32 አመታት እንደ ኢትዮጵያዊ ሁኖ መኖር ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ላቦራቶሪው ገብቶ ውጤቱን ፤ አስከፊነቱን እርም ዳግም አይስፈልገኝም እንድል ያደረገ ነው። ወረቀት ላይ መላምት ማነብነብ ባህር ማዶ ቁጭ ብሎ እና በገሀድ ኢትዮጵያዊ ሁኖ ኑሮ ማየት የተለያዩ ናቸው። ማርክስ ታዋቂ የኢኮኖሚክስ ፈላስፋ ነበር ( በወሬ ብቻ) ግን የሚልስ የሚቀምሰው አጥቶ በመናጢ ድህነት ነበር የሞተው - ምክንያቱም የሚያወራው ቅዥት እንጅ እውነት ሁኖ ፍሬ ስለማያፈራ ነበር። ወያኔዎች እና ኦነጎች እነኝህ አናሳዎች በቀኝ ገዥዎች ጉዳይ አስፈጻሚነት ስለተቀጠሩ ማንም በአለም ላይ ያለ አገር እና ህዝብ የማይጠቀምበት እንዳውም እንደ ወንጀል የሚቆጠር የጎሳ ክልል በኢትዮጵያ አይቀጥልም። ውጤቱ እኮ ለአለም እስኪገርመው ታየ 1.5 ሚልዮን ህዝብ በጦርነት ሲያልቅ። ይህ ነበር ቱርፋቱ።
የሚባለው አክራሪ ትግሬ ዋና አላማው ኢትዮጵያዊ ሆኖ መቀጠል ሳይሆን በማታለለ የኢትዮጵያን መሬት በመንጠቅ ሀገረ ትግራይ መሆን ነው። ለዚህ እኩይ አላማ ደግሞ መከፋፈል እጅግ ጠቃሚ ነው። ታዲያ ህሌና ያለው ሰው ይህንን ሁሉ እልቂት አይቶ ወደ ብጎው እና ሁሉ አለም የሚከተለውን የፓለቲካ እና ስነ መንግስት ይመለሳል እንጅ ወደ ዘር ማጥፋት ስርዐት ልመለስ ይላል?

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by sarcasm » 25 Jun 2023, 08:26

Horus wrote:
23 Jun 2023, 16:42
ሳርካስም፣
አሁንኮ እስከ ሚሰለች የምትደጋግመው ላለፉት 60 አመታት ጉንጫችንን ያለፉት አሰልቺ ድግግሞሽ ነው። የምትለው ፌዴረ እኮ ነው የዘር እልቂት ጄኖሳይዳዊ ሲስተም የሆነው ። መሳይ ከበደ የደቡን ኤትኖ ፌደረ ነው። የሱም ሃሳብ ያረጀ ነው።

ንጉስና ንጉሰ ነገሰ ምንም ከራስ ገዝነት ጋር የሚገናኝ አይደለም ። ፊውዳል ሲስተም ነው ። በፊውዳል ሲስተም አንድ ጉልበተኛ እግዚአብሄር ስለሾመኝ ሕዝቡም መሬቱም የኔ ብሎ ከዘር ዘር ይገዛል ። ሕዝቦቹ ሰርፍ ወይም ባሪያ ይባላሉ ።

በኋላ ሌላ የትግሬን ጉልበተኛ የሚበልጥ ጉልቤ የመጣና ንጉሱ ከባሪያዎቹ ከዘረፈው ግብር እንዲቆረጥለት ያስገድዳል ። ንጉሱ የንጉሰ ነገስቱ ግብር ሰብሳቢ ይሆናል ! ይህን መሰል ፌውዳል ሰፍደምን ነው አንተ ፌደራሊዝም የምትለው ። እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ !! አው ምኒልክ ከአባ ጅፋር ስልጣን አልቀማውም ግ ን አባ ጅፋር ባሪያ ነጋዴ ነበር እንጂ የጂማ ሕዝብ እራሱን የሚገዛ ነጻ ሕዝብ አልነበረም ። ዛሬም አይደለም !! ፒፒ የሚገዛው ዘመናዊ ሰርፍ ነው!

የትግሬን እንተወው !
It seems you are confusing the Neguse Negest governance system with feudal land management system. For example in tigrigna speaking villages where my parents hail from, farmland is communally owned by the village community - there was no feudalism. Members of the village get plots of land according to their family size and when people pass away, the land is returned to the village and their children do not inherit farmlands from their parents. When people get married, the village community build them a house and they get plots of farmland. The system is called መሬት ጤሳ / መሬት ደሳ. People / Villages had total autonomy and they were እራሱን የሚገዛ ነጻ ሕዝብ. There was no feudalism in our part of the land although I have read a lot how feudalism created havoc in South Ethiopia following the spread of Abyssinia southwards.

Selam/
Senior Member
Posts: 11852
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Selam/ » 25 Jun 2023, 09:03

ማርክስ ሲፈጠር ጀምሮ በቀውስና መናጢነት ያደገ እርጉም ነው። ኤንግልስ ፍርፋሪ ባይጥልለት ኖሮ ቀድሞ ይሞት ነበር። ካፒታልን ከተቀበረበት አቧራ አንስቶ፣ አጣሞ ተርጉሞ ዓለምን ያተራመሰው ሌኒን የሚባለው ተውሳክ ነው። የኛዎቹ እንጭጭ ኮሚኒስት ሽሎች ደግሞ ደሃው ህዝብ ላይ አምጥተው ደነቀሩበት ሲያመቻቸውም ህዝቡን ከህዝብ በማጋጨት ለስልጣን ማራዘሚያ ተጠቀሙበት። ባለጊዜዎች አልገባቸውም እንጂ፣ የዘር ፖለቲካ ማንንም አይጠቅምም፣ ሁላችንንም ያናክሰናል፣ በተራ በተራ ይዞን ይጠፋል።
Abere wrote:
23 Jun 2023, 16:59
አዎን የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ethnic federalism ነው። ይህን ሀቅ ለማወቅ ጥልቅ ትምህርት እና ዕውቀት የሚፈልግ አይደለም። ለአለፉት 32 አመታት እንደ ኢትዮጵያዊ ሁኖ መኖር ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ላቦራቶሪው ገብቶ ውጤቱን ፤ አስከፊነቱን እርም ዳግም አይስፈልገኝም እንድል ያደረገ ነው። ወረቀት ላይ መላምት ማነብነብ ባህር ማዶ ቁጭ ብሎ እና በገሀድ ኢትዮጵያዊ ሁኖ ኑሮ ማየት የተለያዩ ናቸው። ማርክስ ታዋቂ የኢኮኖሚክስ ፈላስፋ ነበር ( በወሬ ብቻ) ግን የሚልስ የሚቀምሰው አጥቶ በመናጢ ድህነት ነበር የሞተው - ምክንያቱም የሚያወራው ቅዥት እንጅ እውነት ሁኖ ፍሬ ስለማያፈራ ነበር። ወያኔዎች እና ኦነጎች እነኝህ አናሳዎች በቀኝ ገዥዎች ጉዳይ አስፈጻሚነት ስለተቀጠሩ ማንም በአለም ላይ ያለ አገር እና ህዝብ የማይጠቀምበት እንዳውም እንደ ወንጀል የሚቆጠር የጎሳ ክልል በኢትዮጵያ አይቀጥልም። ውጤቱ እኮ ለአለም እስኪገርመው ታየ 1.5 ሚልዮን ህዝብ በጦርነት ሲያልቅ። ይህ ነበር ቱርፋቱ።
የሚባለው አክራሪ ትግሬ ዋና አላማው ኢትዮጵያዊ ሆኖ መቀጠል ሳይሆን በማታለለ የኢትዮጵያን መሬት በመንጠቅ ሀገረ ትግራይ መሆን ነው። ለዚህ እኩይ አላማ ደግሞ መከፋፈል እጅግ ጠቃሚ ነው። ታዲያ ህሌና ያለው ሰው ይህንን ሁሉ እልቂት አይቶ ወደ ብጎው እና ሁሉ አለም የሚከተለውን የፓለቲካ እና ስነ መንግስት ይመለሳል እንጅ ወደ ዘር ማጥፋት ስርዐት ልመለስ ይላል?

union
Member+
Posts: 6429
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by union » 25 Jun 2023, 09:14

Akaleguzi agame

Ethnic federalzim ለኢትዮጵያ ጥሩ ነው አልሽ? አንቺ low IQ ቆርጫሚ :lol:

Tiago wrote:
23 Jun 2023, 15:27
ሰባተኛ፣
ልክ እንደ ፓርቲ ሃሳብ ፌዴራሊዝም የተባለው አሰልቺ፣ ምን እንደ ሆነ የማይታወቅ ባዕድ ሃሳብ ተሰርዞ ሌላ ከህዝባችን ባህልና ታሪክ የፈለቀ ያስተዳደር ስርዓት ለውይይት መቅረብ አለበት ።

Federalism is not bad for Ethiopia as long as it is not hijacked and mixed with narrow ethnic politics.
ethnocentric politics shrouded in the name of defending ethnic groups from fictional exploitation must be seen not different from Nazism or racism and must be banned altogether.

እብዱ አብይ አሰብን ለማስመለስ የጋላና የአጋሜ ጀሌ ይዞ ይሞክረው

Right
Member
Posts: 2835
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Right » 25 Jun 2023, 10:20

ማርክስ ሲፈጠር ጀምሮ በቀውስና መናጢነት ያደገ እርጉም ነው። ኤንግልስ ፍርፋሪ ባይጥልለት ኖሮ ቀድሞ ይሞት ነበር። ካፒታልን ከተቀበረበት አቧራ አንስቶ፣ አጣሞ ተርጉሞ ዓለምን ያተራመሰው ሌኒን የሚባለው ተውሳክ ነው። የኛዎቹ እንጭጭ ኮሚኒስት ሽሎች ደግሞ ደሃው ህዝብ ላይ አምጥተው ደነቀሩበት ሲያመቻቸውም ህዝቡን ከህዝብ በማጋጨት ለስልጣን ማራዘሚያ ተጠቀሙበት። ባለጊዜዎች አልገባቸውም እንጂ፣ የዘር ፖለቲካ ማንንም አይጠቅምም፣ ሁላችንንም ያናክሰናል፣ በተራ በተራ ይዞን ይጠፋል።
This is by far the best fact based observations. Much of Ethiopia’s administrative policy is still directly copied from a communist system.
Ethiopia will never be able to advance until it gets its land policy right. Basically it was copied from communist Russia without any studies and analysis after the revolution.

Look, many African & S. American countries flirted with socialism in the 60s& 70s but they quickly moved away after they figured out that it was a disaster.
Ethiopia not only stuck with it but it went beyond the norm. Ethnic federalism is a result of that policy.

Abere
Senior Member
Posts: 11143
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Abere » 25 Jun 2023, 11:08

Please do not tamper history. You kind of referring something like a hunting and gathering primitive society. Or a communist version of ownership. Feudalism was a universal socio-economic and governance system that all societies/countries/ under monarchical system experienced and undergone. The smooth evolution from feudalism to industrialization transformed the present day developed countries. The catastrophe of communalization and fragmentation of land prohibited investment and large scale undertakings. In stead, passive and lazy government such as TPLF used it to control farmers and turn them into cadres. ጤሳ is foreign to Amhara provinces of Wollo ( that includes Raya Alamata-Korem), Gondar (that includes Welqait and Humera), Shewa, Gojjam and beyond.

sarcasm wrote:
25 Jun 2023, 08:26
It seems you are confusing the Neguse Negest governance system with feudal land management system. For example in tigrigna speaking villages where my parents hail from, farmland is communally owned by the village community - there was no feudalism. Members of the village get plots of land according to their family size and when people pass away, the land is returned to the village and their children do not inherit farmlands from their parents. When people get married, the village community build them a house and they get plots of farmland. The system is called መሬት ጤሳ / መሬት ደሳ. People / Villages had total autonomy and they were እራሱን የሚገዛ ነጻ ሕዝብ. There was no feudalism in our part of the land although I have read a lot how feudalism created havoc in South Ethiopia following the spread of Abyssinia southwards.

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by sarcasm » 25 Jun 2023, 12:20

Abere wrote:
25 Jun 2023, 11:08

I am not saying the ጤሳ system was used outside the Tigrigna speaking areas or the ጤሳ system is the only land system in Tigrigna speaking part of world. I know families in some parts have a land called መሬት ጽልሚ which means only descendants of a certain family in the village own the plots of land. I am proving that feudalistic land ownership is not inherent element of the Negus and Neguse Negest autonomous / ራስ ገዝ governance system. The federalist Neguse Negest system can exist with egalitarian land ownership system and feudalistic land ownership.

If you think the ጤሳ system is fiction or tampering with history, then I cannot help you. Tbh, I am not even saying it is the best system or it is a flawless system I can list some of the drawbacks of the ጤሳ land management system. But that is not the discussion point here.

Abere
Senior Member
Posts: 11143
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Abere » 25 Jun 2023, 13:59

In general terms, feudalism is related to land and landholding relationships where the landlord owned lands and give to peasants in return to their loyalty and service. That where you have the kingdom. There could be variations among or within regions. However, there are some commonalities. As far as I knew, there were at least three holding arrangements, namely:
1) የገባር መሬት
2) ጋላ መሬት
3) ልዩ ማደሪያ መሬት

The ገባር መሬት is the most common and local people ownership of land. They are required to pay tax. Whereas ጋላ መሬት is given to those who provided military services to the lord, they do not pay tax other than serving. This usually is those landless tenants who used to get land by being recruited as soldier - the term likely taken after 16th century where Oromo mingled with highlander and introduced agriculture. The ልዩ ማደሪያ መሬት was those privilege ranks in the kingdom such as ቀኛዝማች፤ግራዝማች፤ፊታውራሪ፤ ባላባራስ. They do not pay tax too. The tax burden was on the ባላገር folks that was the issue.

The ጤሳ things sounds to me more like village level affairs. It sound ጢስ, for instance every (tukul) tax levy ግብር በጢስ እንድሉ. I am not sure there was a such a striking dissimilarity between Amhara and Tiger as such. In any case, the Derg unwise intervention and half-baked educated groups brought a wrath on the country, the unforeseen effects of which, I would say, irreversible damage to the smooth evolution (progression) of the society. It is very unfortunate, because the country's population already passed 100 million now to do anything.

sarcasm wrote:
25 Jun 2023, 12:20

I am not saying the ጤሳ system was used outside the Tigrigna speaking areas or the ጤሳ system is the only land system in Tigrigna speaking part of world. I know families in some parts have a land called መሬት ጽልሚ which means only descendants of a certain family in the village own the plots of land. I am proving that feudalistic land ownership is not inherent element of the Negus and Neguse Negest autonomous / ራስ ገዝ governance system. The federalist Neguse Negest system can exist with egalitarian land ownership system and feudalistic land ownership.

If you think the ጤሳ system is fiction or tampering with history, then I cannot help you. Tbh, I am not even saying it is the best system or it is a flawless system I can list some of the drawbacks of the ጤሳ land management system. But that is not the discussion point here.

Selam/
Senior Member
Posts: 11852
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Selam/ » 25 Jun 2023, 14:07

በጎጥ ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማይሰራ ያለፉት 30 ዓመታት ውድቀት ካላስተማረህ መቼም አትማርም።
case in point:

- ሃይሉን ስለሚቀንስበት የማዕከላዊው መንግስት ትክክለኛ የፌዴራል አስተዳደር እንዲኖር አይፈልግም። ስለዚህም ፌዴራሊዝምን በጎጥ በመወጠር አንዱን ከአንዱ እያናቆረ እድሜውን ለማራዘም ይሰራል እንጂ ትክክለኛ ራስ ገዝነት እንዲኖር አይፈቅድም።

- የማዕከላዊው መንግስት ለአንዱ ህዝብ ክልል ፈቅዶ ለሌላው መከልከሉ፣ የጎጥ ፌዴራሊዝምን ፉርሽ አድርጎታል። ህገ መንግስቱን እንደወረደ ከተረጎምከው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመቶ በላይ ክልል የማይኖርበት ምክንያት የለም። የከፋው ህዝብ ሁሉ ጥቃቅን የራስ ግዛትን እያወጀ ተበጣጥሶ እንደዝንጀሮ የማይኖርበት ምክንያት የለም። በየመንደሩ የቀበሌ ሹመኛና ካድሬ እንደአሸን ተፈልፍሎ የዚህ ሁሉ ቢሮክራት ስራ ሰው ትከሻ ላይ ተዘፍዝፎ ኢኮኖሚ ከማሳደግ ይልቅ ወረቀት ማገላበጥ፣ ቁጥር መቁጠርና ጊዜን በስብሰባና ወሬ መፍጀት ይሆናል።

- የክልል መንግስት የተባሉትም ከማዕከላዊው የተለየ ባህርይ የላቸውም። የማዕከላዊው መንግስት ስንጣሪ ካልሆኑም በጠቅላዩ እንደተደቆሱ ይኖራሉ። የስልጣን ዕድሜያቸውን የሚያራዝሙትም በስራ ብቃት ስላልሆነ የእኛ አይደሉም የሚሉትን ህዝብ ከማዋከብና አንዱን ከሌላው ከማጋጨት የተሻለ አሰራር አይኖራቸውም። በጎጥ የከረረውም ህዝብ ከራሱ ቋንቋና ወንዝ ውጪ ሌላ ዓለም ያለ ስለማይመስለው በአስተሳሰብ ከመስፋፋትና ከሌላው ጋር በገበያና ማህበራዊ ኑሮ ከመተሳሰር ይልቅ ወደ ውስጥ እየጠበበና እየቀነጨረ ይሄዳል። እንደ ትውልድ መደንቆርና መጨንገፍ ማለት ይኸ ነው።

Tiago wrote:
23 Jun 2023, 15:27
ሰባተኛ፣
ልክ እንደ ፓርቲ ሃሳብ ፌዴራሊዝም የተባለው አሰልቺ፣ ምን እንደ ሆነ የማይታወቅ ባዕድ ሃሳብ ተሰርዞ ሌላ ከህዝባችን ባህልና ታሪክ የፈለቀ ያስተዳደር ስርዓት ለውይይት መቅረብ አለበት ።

Federalism is not bad for Ethiopia as long as it is not hijacked and mixed with narrow ethnic politics.
ethnocentric politics shrouded in the name of defending ethnic groups from fictional exploitation must be seen not different from Nazism or racism and must be banned altogether.

እብዱ አብይ አሰብን ለማስመለስ የጋላና የአጋሜ ጀሌ ይዞ ይሞክረው
Last edited by Selam/ on 25 Jun 2023, 17:51, edited 5 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሆረስ ሃሳብ ፤ Post-Abiy Political Wisdom

Post by Horus » 25 Jun 2023, 14:40

አበረ፣
ትግሬዎች ጤሳ የሚሉትና አንተ ጢስ ያልከውኮ ትልቁ ጢሰኛ የሚባለው ሲስተም ነው። አንድን ቤት ዳስ፣ ደሳ፣ ገዛ አልነው ያ ነበር ጢሰኛ የሚባለው ። እንዳልከው የድህረ የካቲት የኢትዮጵያ መሬት ስሪት ከላይ እስከ ታች ለብዙ አመታት የተጠና አንድ ሙሉ ትውልድ ክርክር ያደረገበት ብዙ ቫሪዬሽን የነበረው ጉዳይ ነው። አሁን እዚያ አንሄድም።

ትልቁ ስህተተ መሬት የንጉስ ነው ከሚለው መሬት የመንግስት የሚለው ነበር/ነው ። ዛሬ ያን ይዘው ነው የወያኔና ወረሙማ ሌቦች መሬት የክልል መንግስት ነው በማለት አንድን ጎሳ ከሌላ ክልል የሚያባርሩት ።

መሬትን የፈጠረ እግዚአብሄር ነው ። ይህ እግዚአብሄር የፈጠረውን መሬት የሰው ልጅ እንዴት ማኔጅ ያድርገው ሲባል ንጉሳዊ ስርዓት ምን ቢል ይሻላል? ንጉስ በእግዚአብሄር ተቀብቶ ስለተሾመ የመሬቱን ባለቤትነት ለንጉሱ ሰጥቶታል ተብሎ የመሬት ባለቤት ንጉሱ ሆነ ።

ሶሻሊስቶች ንጉስ ማለት (ያገር ገዢ) መንግስት (እስቴት) ስለሆነ ያገር ንብረት ሁሉ የመግስት ነው የሚላ አዲስ አይነት ፊውዳሊዝ አመጣ ። ዛሬ የዚያ ጣጣ (መሬት የመንግስት ነው የሚለው) የጎሳ መንግስት ተብዬ ሁሉ ኬላ እያቆመ የዘረፋና የሽፍቶች አገዛዝ ያስፋፋው ። ኢትትዮጵያ ከዚህ መላቀቅ አለባት ።

እንዲያውም ትልቁ የፌዴሬሽን ውዥንብር የፖለቲካ ይዘቱ ነው ። አንድ ሕዝብ የፖለቲካ ስርዓት ፈጥሮ ፖለቲካዊ ማህበረ ሰብ ሲሆም ብቸኛ ወሳኝ መቆሚያው ምንድን ነው ሲባል ዝም ብሎ ሕዝብ፣ ቡድን፣ መደብ ጎሳ ክላን ወይም ቤተ ሰብ ሳይሆን አንድ ግለሰብ፣ አንድ የሰው ልጅ፣ አንድ ዜጋ ነው ።

የሰው ልጆች ስርዓት መነሻ ፕሪሚስ፣ ፋውንዴሽን አንድ ሰው ምንድን ነው? መብቱ ምንድን ናቸው? ግዴታው ምንድን ናቸው? በሚሉት የአንድ ሰው እንደ ራስ ገዝ ፣ ራስ አስተዳድሪ ፣ ነጻና አውቶኖመስ ህልና በማረጋገጥ ላይ የሚገነባ ሲስተም ነው።

ልክ አንድ የእጁ ሰራ ውጤቶች የራሱ ንብረት እንደ ሆኑ ሁሉ እግዚአብሄር በተጠረው መሬት ላይ የሚፈጥረው በረከት ንበረት እንዲሁ የራሱ ናቸው ። አንድ ሰባዊ ስርዓት ባለበት አገር አንድ ነጻ ዜጋ መሬት እንዴት መያ፣ በግዛት፣ መሸጥ፣ መለወጥ፣ ማምረት በሚሉት ላይ ህጎች ይኖራሉ እንጂ ነጻ ዜጋዎች መሬት መያዝ፣ መጠቀም ፣ ንብረታቸው ማድረግ አይችሉም የሚል ሕግ ሊኖር አይችልም ። ያን ስልጣም ያለው እግዚአብሄር እንጂ መንግስት አይደለምና ።

መንግስት አስተዳዳሪ እንጂ መሬትን የፈጠረ ኃይል አይደለም ።

በተምሳሳይ ራስ ገዝነት እንዲህ ከጎሳና ቡድን የወል መብት ጋር ያለው ውዥንብ ነው ። የዘመናዊ ፖለቲካ ሃ ሁ መጀመሪያ ራስ ገዝ፣ ነጻ ሰው፣ ነጻ ግለሰብ እንጂ ራስ ገዝ ካልን፣ ራስ ገዝ ቡድን፣ ራስ ገዝ ጎሳ ፣ ራስ ገዝ ብሄር አይደለም ። ራስ ገዝ ጎሳና፣ ብሄር ወዘተ የሚያቆሙት ነጻ ግለሰቦች፣ ነጻ ዜጋዎች ናቸው ።

ነጻ ዜጋ በሌለበት ወረሚያ፣ ትግሬ ወይም ጉራጌ ክልል ራስ ገዝ ወረሞች፣ ራስ ገዝ ትግሬዎች ወይም ራስ ገዝ ጉራጌዎች ሊኖሩ አይችልም ። ያ ከሆነ ክልልሉ የባርነት ስርዓት ይሆናል ማለት ነው ። ስለዚህ ፌዴራሊዝም የሚባለው ጥንቆላ የሰፊ አገር ማስተዳደሪያ ዘዴ እንጂ የአንድ ሕዝብ ሰባዊና ፖለቲካዊ መብቶች እና ስልጣኖች የሚመነጩት አንድ ግለሰብ እንደ ነጻ ዜጋ ባለው የተፈጥሮና ማህበራዊ መብትና ነጻነቶች ነው ።

Post Reply