Page 1 of 1

በታሪክ የብዙዎች ቀደምት የሆነችዉ ኢትዮጵያ ቀጣይነትን ማስቀደም እንዴት ኣቃታት?

Posted: 26 Mar 2024, 02:12
by Naga Tuma
ቀጣይነት ያልኩኝ ኮንቲኒዩቲ ለማለት ነዉ። በኦሮምኛ ፉፍንሰ ማለት ነዉ። አባት ልጁን ፉፋ ሲል ባዮሎጂካል ኮንቲኒዩቲን ለማመልከት ነዉ።

ኢትዮጵያ ከብዙዎች የቀደመ ታሪክ ኣላት።

በዓለም ላይ ክርስትና፣ የቫቲካን ልዕልና፣ እስልምና፣ የእንግሊዝ የዙፋን ልዕልና፣ እና የኣሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ መሪነት ቀጣይነታቸዉን ኣስተካክለዉ ያስቀመጡ ምሳሌዎች ናቸዉ።

የኢትዮጵያም ሆነ የአከባቢያችን ታሪክ ከእነዚህ ሁሉ የቀደመ ነዉ።

ፒራሚድ የሰሩት ቀጣይነትን ኣላሳዩም።

የአክሱምን ሃዉልቶች የሰሩት ቀጣይነት ተዳከመ።

የንግስት ሳባ ልዕልና ኣልቀጠለም።

የዛጉዌ ስርዓት ኣልቀጠለም።

የኩኖ ኣምላክ መልሶ ያቆመዉ እንደገና ተዳከመ።

ኣጼ ቴዎድሮስ ለፍተዉ ኣቁመዉ ተሰዉ።

ኣጼ ምንልክ የቀጠሉት እንደገና ተዳክሞ በኣጼ ሀይለስላሴ ቢጠነክርም ኣብዮት ናደዉ።

ብያንስ በሃገር ቀጣይነት ላይ ሁላችንም መስማማት ሲቻል በጎሰኝነት ላይ ክርክር እስከዛሬ ድረስ ኣለ።

የትኛዉም ይሁን ቀጣይነቱን ያስተካከለ አመራርም ሆነ አከባቢ ቢኖረን ምሳሌ ይሆነናል።

ለቀጣይነቱ ሕገመንግስታዊ ዋስትና ያላስተካከለ ሃገር ሃገር ነኝ ማለት ይችላል?

ለኢትዮጵያ ቀጣይነት ፈተና በብዛት የውጪ ጫና ነዉ። ለምሳሌ የግራኝ መሃመድ ዘመን።

ነገር ግን ሁሉንም በዉጪ ጫና ላይ ማሳበብ ይቻላል? ለምሳሌ ስለዚህ ዘመን የጎሰኝነት ፉክክር።

ክርስትና፣ ቫቲካን፣ እንግሊዝ፣ እስልምና፣ እና አሜሪካ ከኢትዮጵያ በኋላ ተነስተዉ ቀጣይነታቸዉን ካረጋገጡ ኢትዮጵያ እንዴት ኣቃታት?

Re: በታሪክ የብዙዎች ቀደምት የሆነችዉ ኢትዮጵያ ቀጣይነትን ማስቀደም እንዴት ኣቃታት?

Posted: 26 Mar 2024, 03:01
by Horus
ናጋ ቱማ፣

ተሳስተሃል ።

አንተ ዛፉን እንጂ ጫካውን አላየህም ።

ጫካ ቀጣይ ነው፤ በጫካ ውስጥ ያሉት ዛፎች ሁሉም በግዜ ወድቀው ይሞታሉ ።

ስለዚህ መጀመሪያ የአገር ህልውና የሚከሰተው በቀጣይነት ብቻ አይደለ ።

አገር ይቀጥላል ። ያድጋል ወይም ያንሳል፤ አገር ይለወጣል ወይም አዲስ አገር ይሆናል ።

አገር ታሪክ ነው ። እያንዳንዱ የታሪክ አይነት ፤ መቀጠል፣ ማደግ፣ ማነስ ፣ መለወጥ ፣ መፈጠር የራሳቸው ሂደት አላቸው ።

ኢትዮጵያ እንደ ጫካ ይሀው 3 ሺ አመት አለች ፣ የውስጧ ዛፎፍ ግን ሁሉም በሚባል ደረጃ የቀጠሉ አሉ፣ የጠፉ አሉ፣ ያደጉ አሉ፣ ያነሱ አሉ፣ የተለወጡ አሉ፣ አዲስ የተፈጠሩ አሉ ።

ለምሳሌ ዛሬ ግራ ተጋብተው ከሁሉም ጋር እየተጋጩ የቆጥ የባጡን የሚይዙትና የሊለቁትን እነአቢይን ተመልከት ።

እነዚህ ሰዎች ለግዜጂ ነገሮችን የመወሰን ኃይል መያዛሸውን እንጂ ጫካና ዛፉ፣ የታሪክ ምስጢርና ፍሰት፣ ወዘተ ብዙም አልገባቸውም ። ሊገባቸውም አይችልም ።

ዛፍ የሚኖርበትን ጫካ ማየት አይችልም ። አሳ የሚኖርበትን ውቂያኖስ ማየት አይችልም ።

አቢይ፣ አዳነችና ሺመልስ ዛፎች ናቸው ። ያቢይ አይን ከቤተመንግስት አልፎ አያይም ። ያዳነች አይን ከማዘጋጃ ቤት ፣ የሺመልስ ከአዳማ ። ሁሉም ዛፎች ስለሆኑ!

የኢትዮጵያን ጫካ ለማየት ከመንደር ዛፍነት የመመንጠቅ ችሎታ ይሻሉ፣ ያ ደሞ በታክቲክ አይመጣም ፣ ታሪክ ሆኖ በሂደት በዘመናት ጫካነት የሚመጣ ማንነት ነው ።

ጫካው ፌክ አይደረግም ፣ ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል ።

ስለዚህ ኢትዮጵያ ለ3 ሺ አመት ስለቀጠለች ነው ይህው ዛሬ በውስጧ እየኖርን ስለሷ ኢ አር ላይ የምንወያየው ።

ኢትዮጵያ የለችም የሚሉት ትክክል ናቸው ! ዛፎች ስለሆኑ ጫካውን በፍጹም ማየት አይችሉም ! አሳዎች ናቸው የሚኖሩበትን ውቂያኖስ በፍጹም ማየት አይችሉም !

ያ ነው የጎሳው ዛፍ፣ ያ ነው የጎሳው አሳ ኢትዮጵያን ማየት ያልቻለውና የማይችለው !

ይህው ዛሬ በአስርት ሚሊዮኖች የሚቆጠር ጎሰኛ ኢትዮጵያ የለችም እያለ ግ ን በውስጧ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ፓስፖርቷን ተሸክሞ ይኖራል ። ዛፍ ነውና ጫካውን ያይ ዘንድ ፈጽሞ አይችልም ።

ዛፍ ከመሆን ተለውጦ ከፍ ያለ ምድር ላይ ቆሞ ጫካውን ከላይ ከልተመለከተ በተቀር !

ኢትዮጵያ ገና ለሺዎች ዘመታ ትቀጥላለች !! ዛፍ ይበቅላል! ዛፍ ይሞታል!