Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5552
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: መለኮት፣ ባህል፣ ሳይንስ፥ ሬይነሳንስ 101 ለሆረስ

Post by Naga Tuma » 25 Apr 2024, 15:12

I wish I could use the time for something else. You have failed over and over to explain a simple observation about ancient history, which is my point.

የራስህን የጥንት ታሪክ ቤት ስራ በትክክል ሰርተህ የነበረ ቢሆን ሌላ ቤት ስራ እንድትሰራ ምን ኣለፋኝ? ኣዉቃለሁ ብለህ የዘረገፍከዉን ቢ ኤስ እንኳን ማጽዳት ኣልቻልክም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5552
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: መለኮት፣ ባህል፣ ሳይንስ፥ ሬይነሳንስ 101 ለሆረስ

Post by Naga Tuma » 25 Apr 2024, 15:49

ጳዉሎስ ሮም ሄዶ ስለቤተልሔም ያስተማረዉ ዐይነት ትምህርት ጋር የሚመሳሰል ትምህርት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር?

በእኔ ግምት ኣባ ሰላማ ኢትዮጵያ ደርሶ ስለቤተልሔም ያስተማረዉ ተመሳሳይ ነዉ።

ይህ ግምት እዉነታ ያለዉ ከሆነ ቁልፍ ጥያቄ የሚሆነዉ በአከባቢያችን ታሪክ ዉስጥ እንደ ዲ ሪረም ናቹራ የምናየዉ ምንድነዉ?

ሆረስ፥

ጥንት ግብጥ ከዲ ሪረም ናቹራ መጻፍ በፊት እጅግ ጥንት መሆኑን ከኣወክ የጥንት ግብጥ ዲ ሪረም ናቹራ ይህ ነዉ የምትለዉ ኣለህ? ኣዎ ወይም ኣይ የሚል ቀላል መልስ በቂ ነዉ።

ለዚህ ጥያቄ ግዙፍ ስህተትህን ባላነብ እንድታዉቅ ኣልለፋም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5552
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: መለኮት፣ ባህል፣ ሳይንስ፥ ሬይነሳንስ 101 ለሆረስ

Post by Naga Tuma » 26 Apr 2024, 17:59

ሆረስ፥

ይህ ርዕስ በቂ ማብራርያ ኣግኝቶ የሚገባደደዉ እንደ ኢትዮጵያ ዲ ሪረም ናቹራ የምናየዉ ይህ ነዉ ማለት ሲቻል ነዉ።

ለዚህ ታሪካዊ ጥያቄ በቂ መልስ ስታገኝ ነዉ የኢትዮጵያን ታሪክ በበቂ ጥልቀት ኣዉቃለሁ ማለት የምትችለዉ። በእኔ ግምት ከብዙዎች ባላይ የቀረብክ ነህ። ለዓመታት ያስተዋልኩኝ እስከመሰረቱ ያልዘለክ መሆንህን ነዉ፣ የጻፍከዉን ኣንብቤ።

ለዚህ እኔ እንደገባኝ ፍንጭ ነዉ ብዬ የማስበዉን እንደገና ላካፍልህ።

ለመነሻ እንዲሆን የሰዉ ዘር ከተፈጠረ ግዜ ጀምሮ ከሰዉ ያልተለዩትን ሁለት ክስተቶችን ማስታወስ በቂ ናቸዉ፥ መወለድ እና ህይወት ማለፍ።

ለህይወት ማለፍ ክስተት የሰዉ ዘር በረጅም ታሪኩ ዉስጥ እንዴት ሲገነዘበዉ ኖረ?

ሶስት ግንዛቤዎችን በደንብ ማስተዋል በቂ ፍንጮች ይሆናሉ ብዬ ኣስባለሁ።

1)ኛ) ቦረና ዉስጥ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ግንዛቤ
2)ኛ) የኢትዮጵያ ተዝካር ባህል
3)ኛ) ዲ ሪረም ናቹራ ዉስጥ ያነበብከዉ ዋነኛ ነገር

ስለተዝካር ባህል እና ዲ ሪረም ናቹራ በደንብ ታዉቃለህ ብዬ ኣስባለሁ።

ቦረና ዉስጥ ስለሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ግንዛቤ የሰማሁትን እንደገና ላካፍል።

ከብዙ ዓመታት በፊት የቦረና ማህበረሰብ ዕዉቀት ጠባቂ ነዉ የተባለ ሰዉ እዚህ ኣሜሪካ መጣ ተብሎ ፈልጌ ኣግኝቼዉ ነበር። መሠረታዊ ስለሆኑ ነገሮች ባህላዊ ግንዛቤዉን ለማወቅ። ስሙ ደበሳ ጉዮ ይባላል።

የመጀመርያዉ ጥያቄዬ የሰዉ ህይወት ስያልፍ ምን ይሆናል ነዉ።

አጭር መልስ ነዉ የሰጠኝ። ዋቀ መሌ ነምን ህን ቤኩ። ነምን ነን ቤከ ጄቹን ጩቡ ዻ።

ትርጉሙም የምያዉቀዉ ዋቀ ነዉ፣ ሰዉ ኣያዉቅም። ሰዉ ኣዉቃለሁ ማለት ጩቡ ነዉ እንደማለት ነዉ። ጩቡ የጉራግኛ ቃልም እንደሆነ ነዉ የሚገባኝ።

ያን መልስ ከሰጠኝ በኋላ በርዕሱ ላይ ብዙ ግዜ ኣላጠፋንም። ስለ ገነት እና ገሃነም እንደሚታወቅ ጨምሬ ስጥይቀዉ ሰዉ ኣርፎ በኣርባኛዉ ቀን ዋቀ ጋ ቀርቦ ዋቀ ፍርዱን ይሰጠዋል ኣለኝ።

ያንን መልሱን ስሰማ በዉስጤ ለኣርባ ቀናት ማን ኣብሮ ተጉዞ ኣየ እያልኩ ኣርባ የላዉን ቁጥር ሳስታዉስ ሆሊ ግሬይል ኣልኩኝ። ምክንያቱም በተዝካር ባህል ዉስጥ የኣርባ ቀን ተዝካርም እንዳለ ስለማዉቅ ነዉ።

በእኔ ግምት ይህ ምናልባትም አባ ሰላማ ኢትዮጵያ ሰይደርሱ በፊት የነበረን ተመሳሳይ ባህል ኣመልካች ነዉ። ግምቱ እዉነታ ያለዉ ከሆነ ምናልባትም ቦረና ባህሌን ብሎ ይዞ የሰነበተዉን ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም እኛም ያንን ባህል ነዉ ኣደራጅተን ይዘን የዘለቅነዉን ማለት የሚችል ይመስለኛል።

ይህ ደግሞ የበለጠ የምያግባባ እዉነታ እንጂ የምያከራክር ኣይመስለኝም።

እዚህ ፎረም ላይ ከኣንተ ጋር ለዓመታት የዘለቀ ኣንድ እና ብቸኛ ክርክሬ ኣንተ ቦረና የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ሸዋ ደርሰዉ የማያዉቁ ናቸዉ። ይህን ኣለማለት የምያወሩትን ኣለማወቅ ነዉ ብለህ አፍህን ሞልተህ መጻፍህ ነዉ።

ምናልባትም ከስግመንድ ፍሪዩድ የበለጠ የአባ ባህሬይን መጽሓፍ እንደሳይንሳዊ ጽሑፍ እጅግ ኣንብበህ ይሆናል።

ለኢትዮጵያ ዲ ሪረም ናቹራ ፍንጮች ናቸዉ ብዬ የማስበዉን እና ቦረና መሠረታዊ መሆን ለምን እንደሚችል እጨምራለሁ። የተሻለ ካለም ደስ ብሎኝ እማራለሁ።

Post Reply