Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 31000
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በቴ ኡርጌሳን ማን ገደለው?

Post by Horus » 11 Apr 2024, 02:09

የሚያስገድሉት ምክንያቶች ...

(1) አንድ እጅግ አደገኛ ምስጢር ስለሚያቅው..

(2) በሆነ ሰው ስልጣን ላይ ከፍተኛ አደጋ ስለሆነ ..

(3) በሆነ ሰው አላማ ላይ ጋሬጣ ስለሆነ ..

(4) ሌሎችን ማስተማሪያ ማስጠንቀቂያ ስለሆነ ነው ።

(5) በመቂ ፒፒ ድጋፍ የተነፈገ ስለሆ

በቁጥር 1 መሰረት በቴ መጥፋት መደምሰስ መደለት ያለበት መረጃ ወይም ኢንፎርሜሽን ነው ። ስለዚያ መገደሉ መረጃውን ማጥፋት ማለት ነው ። ይህን አደገኛ መረጃ የማጥፋት ሞቲቭ ያላቸው አቢይ አህመድ፣ ሺመልስ አብዲሳ፣ ሸኔ ወይም አንድ የኦሮሞ ኦሎጋርኪ ናቸው ።

በቁጥር 2 መሰረት በቴ ስልጣን የመቀማት አደጋ ሊያነሳ የሚችለው በራሱ ኦነግ ውስጥ እና ምናልባት በሺመልስ የኦሮሞ መንግስት ውስጥ ይሆናል።

በቁጥር 3 መሰረት በተለያዩ የኦሮሞ ጎሳዎች መሃል የመሬትና ስልጣን ሽሚያ ትግል ሳቢያ እሱ ያለበት የገላን ሜጫ ፣ አሩሲ ቡድን ከጂማውና ከቱለማው ቡድን ጋር ያለ የውስጥ ፍትጊያ ነው።

በቁጥር 4 ሌሎችን ለማስተማር በቴን የሚገድል አንድም አቢይ አህመድ ሌላም ሸኔ ይሆናል።

በቁጥር 5 አቢይ አህመድ በመቂ የድጋፍ ሰልፍ ተከልክሎ ከሆነ ያቢይ ሪቬንጅ ግድያ ሊሆን ይችላል ።

ይህ ሁሉ ሲደመር፣ ገድዮቹ
አንደኛ አቢይ ወይም
ሁለተኛ ሺመልስ ወይም
ሶስተኛ ሸኔ ወይም
ሶስተኛ ተቅናቃኝ ኦሮሞ ጎሳ አሩሲ ወይም ቱለማ ናቸው


Horus
Senior Member+
Posts: 31000
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በቴ ኡርጌሳን ማን ገደለው?

Post by Horus » 11 Apr 2024, 15:11

This is really interesting. ይህ ሰው የአቮካዶ እርሻውን ለማየት ነበር መቂ የሄደው! ኦሮሙማ ሁሉ የአቮካዶ ከበርቴ እየሆነ ነው።

እናም ሰውዬው በወንድሙና እህቱ ነው የተገደለው የሚባለው! የመሬትና ያቮካዶ ውዝግብ ነው ማለት ነው! ወይ ጉድ!


Post Reply