Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4102
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

በኦሮሚያ በተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙ

Post by Za-Ilmaknun » 03 May 2024, 13:04

:mrgreen: Slowly but surely
በኦሮሚያ ክልል በ18 የተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ። ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ እንደሚያስረዳው የክልሉ ንግድ ቢሮ በቄለም ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ አርሲ፣ ቢሾፍቱ፣ ሸገር፣ ነቀምቴ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ፍቼ፣ ሞጆ፣ ሆለታ እንዲሁም ወሊሶ አካባቢዎች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እንዳጋጠመው በመግለጽ ለነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንና ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት መሥሪያ ቤቶች የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል።

በክልሉ የተፈጠረው የነዳጅ እጥረትን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ‹‹እጥረቱ በቢሾፍቱ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኦሮሚያ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ የተፈጠረ ነው፣ ሁኔታው እኛንም አስደንግጦናል፤›› ብለዋል።

እጥረቱ ያጋጠመው በተለይ ትልልቅና የክልሉን የነዳጅ ፍጆታ እንዲጨምር ያደረጉ የልማት ፕሮጀክቶች ማጠናቀቂያ በሆነበት አሁን ላይ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ እንዳደረገባቸው ገልጸዋል።

ችግሩ እየተባባሰ የመጣ መሆኑን የገለጹት እኚህ የክልሉ ከፍተኛ አመራር የአቅርቦት ሁኔታው መንገጫገጭ ከጀመረ ወደ 20 ቀን ማሳለፉንና አሁን ግን ጫናው እጅግ ከፍ ማለቱን አሳውቀዋል።

‹‹ቢሾፍቱ ከተማ የኮንፍረንስ፣ የቱሪስት፣ ብዙ ፋብሪካዎች የሚንቀሳቀሱበት፣ ሪዞርቶች በብዛት ያሉበት ከመሆኑ የሚመለከታቸውን ሁለቱን የመንግሥት ተቋማት ችግር ገጥሞናል፣ እባካችሁ ቶሎ ፍጠኑልን እያልን ነው፤›› ብለለዋል።

ቢሾፍቱ ከተማ ብቻ በየቀኑ አሥር የናፍጣና አምስት የነዳጅ ቦቴዎች እንደሚያስፈልጉት ከከተማው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ነገር ግን ለአጠቃላይ ከተማው ነዳጅ የሚያቀርቡት ሁለት ነዳጅ ማደያዎች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ሔኖስ ወርቁ እጥረቱን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ጥያቄ እንደተነሳላቸው የገለጹ ሲሆን ችግሩ ግን በቢሾፍቱ ከተማ ብቻ የተወሰነ አይደለም ብለዋል።

https://www.ethiopianreporter.com/129155/