Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 11775
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 03 Dec 2024, 14:56
ኦሮሞን ሰፉ ቀበ፣ ይላል አንድ የቆየ የአፋን ኦሮሞ አባባል። ሰፉ ማለት፣ የተፈጥሮ ሕግ እንደማለት ነዉ፣ ሰፉ ገደብ እንድትገዛ ያዛል፣ ያግዳል፣ ሰፉን ተላልፎ የተገኘ ሰዉ በህግ ብቻ ሳይሆን፣ በባሕልም የተወገዘ ይሆናል፣ የተረገመ ይሆናል፣ ሰፉን መተላለፍ የተከለከለ ነዉ።
ይህ ሰፉ አሁን ላይ የምዋጉ ሐይሎችን የገዘ ይመስላል። ኦሮሞ ወደ መንገድ ወጥቶ ሰፉ ይኑራችዉ ብሎ አዘዘ፣ ይህን የሰማ የሸኔ ቡድን ደግሞ፣ አዎ ሰፉን ተላልፈን የትም አንደርስም ና ወደ ሕዝባችን እንመለስ አሉ። ገቡ፣ ለሕዝቡ ሰፉ ብሎ ትጥቃቸዉን እንደ ፈቱ ገለፁ። ጃል ሳኚ ይህን በግልፅ ገልፆታል።
የኦሮሞ ሰፉ ዝም ብሎ የምደሰኩር ሳይሆን፣ በግልፅ ሕብረተሰቡ ላይ ትልቅ ተፅኖ ያለዉ መሆኑን ግልፅ አድርጎታል።