Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11311
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለም።

Post by Abere » 28 Apr 2024, 14:22

DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? አንድ ተምሬያለሁ ያለ እንደ አንተ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ። አማርኛ ውስጥ እንድህ አይነት ቃል ግን የለም ስለው እርሱም አጣ።

ጥያቄ ያልሆነ መልስም የሌለው በድን ጥያቄ 50 አመታት ይዛችሁ የትም መድረስ አላቻላችሁም - አማራ ኦሮሞን በዚህ ስም በዛ ስም ይጠራዋል በሚል የውሸት ክስ። ባለቤቱ የሚጠራበትን የእርሱን ስም አማራ ያወጣለች በማስመሰል ይህም ስም ያልተመለሰ የኦሮሞ ጥያቄ ተብሎ ይጮህበታል። የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ኦሮሞ ከሌሎች 84 ጎሳዎች የተለየ ጥያቄው ወይም ልዩ ጥቅም ከየት ነው የመነጨው - ከሰማይ የወረደ ነው ወይስ ምን ልዩ መብት ነው? ልዩው መብት ልዩ ችግር እንዳይፈጥር ጥያቄው ምንድን ነው እውነት አማራ ኦሮሞን ** ብሎ ሰይሞታል ወይስ ኦሮሞ እራሱን ** ብሎ ይጠራል?

የማጭበርበር ክስ አይመስልህም ወይ? የመንጋ ክስ በፍትህ መንበር ቀጥ ብሎ መቆም አይችልም።

Horus
Senior Member+
Posts: 31066
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Horus » 28 Apr 2024, 15:26

አበረ፣
ልጆች ሆነን የሚነገር አንድ አባባል ነበር ፤ እሱም 'የኦሮሞ ጥያቄ አማራ መሆን ነው' የሚል ነበር! ዛሬ ላይ ይህ ለመለወጡ ምልክት አናይም ።

Abere
Senior Member
Posts: 11311
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Abere » 28 Apr 2024, 16:40

ሆረስ፤

አማራ እኮ የከለከለ አልመሰለኝም። አቶ አብይ አህመድ እኮ ጠቅላይ ሚንስትር እንድሆን የአንበሻውን ድርሻ ጥረት ያደረጉት አማራዎች ናቸው። ብቻ ሰላም፤እኩልነት፤ፍትህ አምጣ እንጅ ሺ አመት ግዛን በማለት ሙሴ እያሉ ዘምረዋል በሌለበት መቀመጫ መንበር ዙፋን ሰርተው ተሸክመዋል። አብይ አህመድ ግን ሰንበትበት ብሎ ሰበርናቸው፤ እኛ ዝሆንነን ጥንቸሎችን እንደፈጥታለን እያለ ወዘተ ቀረሸ። አማራም ግዛኝ ግዛኝ ብለው ሊሸጠኝ አሰበ ነው እንደ ነገሩ በማለት አምላኩን ይዞ ወደ አብይ ዘመተበት - ይኸው የኦሮሙማ መንግስት ስልጣን አልባ ሁኗል በአማራ ክፍለ-ሀገር። አታሞ በሰው እጅ ሲያዩት ያምራል በእራስ ሲይዙት ያደናግራል ይሉ ዘንድ ኦሮሙማዎች አማራ መሆን ቢመኙም አገርን አንድ አድርገው በፍቅር በአንድነት፤ በሰላም እና በመግባባት ማስተዳደር አልቻሉም። ኦሮሙማ ለማስተዳደር ከሚፈልገው አገር ምንም አስተዳዳሪ መሪ የሌለው አገር ይሻላል።

Horus wrote:
28 Apr 2024, 15:26
አበረ፣
ልጆች ሆነን የሚነገር አንድ አባባል ነበር ፤ እሱም 'የኦሮሞ ጥያቄ አማራ መሆን ነው' የሚል ነበር! ዛሬ ላይ ይህ ለመለወጡ ምልክት አናይም ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5569
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Naga Tuma » 29 Apr 2024, 01:48

አበረ፥

ለጠየከዉ በቂ መልስ ኣለኝ ባልልም ወይም ተገቢ መልስ ሰጪ የተጠየቀዉ ቢሆንም የእኔ ግምት ወይም መላምት ላጫዉትህ። ጫወታዉ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ቦረነ፣ ገበሮ፣ ሲዳመ የሚባሉ ጎሳዎች እንጂ ኦሮሞም ሆነ አማራ የሚባሉ ጎሳዎች በሰፊዉ ካልታወቁበት ሰፈር ነዉ።

ኣጼ ሀይለስላሴ ሃገር ለማጽናት እና ለማቅናት ሲለፉ እስቲ ጠበል ያለበት መናፈሻ ልሂድ እና ትንሽ ዕረፍት ልዉሰድ ሲሉ አምቦ ወሰዷቸዉ።

ጠበሉንም አየሩንም ወደዉ ለመናፈሻ ዉብ ቤተመንግስት ክዳነምህረት የተባለች ዉብ ቤተክርስትያን አጠገብ ኣሰርተዉ ሃገረ ህይወት ኣሏት።

ከተማዋን እንድያሳድግ ቁምላቸዉን ሹመዉ ለአስተዳዳሪነት ላኩ።

ኣዲሱን ስም እና ሹመት የሰሙት ነዋሪዎችዋ ኣጼ ኬኘ፣ ኣጤ ኬኘ፣ አት ኬኘ፣ አት የኛ እያሉ የምናዉቃት አምቦ ስም ተቀየረብን ይላሉ።

ተወያይተን የከተማችን ኣስተዳዳሪ ቆሞኬኘ ይሁን ቁምላቸዉን መሾም ልምድ እያለን ቁምላቸዉ ተሾመልን ይላሉ።

ጥያቄዉ ኣጼ ጋ ደርሶ ሰበ ኬኘ፣ እኔ ስለወደድኳት ነዉ ሃገረህይወት ያልኳት እንጂ እናንተ አምቦ ሆና ትቆይ፣ ወይም ኣምባ ትባል፣ ወይም ኣዲሱ ስሟ ይጽደቅ ብላችሁ ተወያይታችሁ ብትወስኑ መብታችሁ ኣይዴለም እንዴ ማለታቸዉን ኣልሰማሁም ወይም ኣላነበብኩም።

ቆሞኬኛ ሆነ ቁምላቸዉ እኔ ሃገር ለማቅናት ስለፋ ኣጋር ከሆነኝ ደገፈኝ እንጂ ምን በደለኝ ማለታቸዉንም ኣልሰማሁም ወይም ኣላነበብኩም።

ብሪታንያ ባህር ተሻግራ ቅኝ ስለመግዛት ኣንብቦ የነበረዉ የኣጼ ሀይለስላሴን ከአዲስ አበበ አምቦ ሄዶ ስም መቀየር እና ተሿሚ መላክ ወሬን ሲሰማ ይህማ ቅኝ ገዢነት ነዉ ብሎ ኣምርሮ ሲለፋ ኖረ።

ተባብረን ሃገር ኣቁመን፣ አድዋ ላይ ኣብረን ተፋልመን፣ ለኣጼ ምኒልክ ቤተመንግስት መሰራት ኣጠና ኣበርክተን፣ ቤተመንግስቱን ተሹመን ኣስተዳድረን፣ ሃገር ለበቀል ዳግም ሲወረር ኣብረን ሸፍተን፣ እንዴት ይህማ ቅኝ ገዢነት ነዉ ትላለህ ሲባል እኔ ታጋይ፣ ኣንተ ተባባሪ ብሎ የበለጠ ኣመረረ።

ተባባሪ ተብሎ የተወቀሰዉም ኣፍርካዊ ሆነህ በኣፍርካ ጉዳይ ተባባሪ ትለኛለህ? የብሪታንያን ኣፍርካ ቅኝ ገዢነት ከኣፍርካ ገለል ለማድረግ የለፉትን ኢትዮጵያ ዉስጥ ቅኝ ገዢ ትላቸዋለህ ብሎ ሲከራከር እና ሲመክር ኖረ።

በዚህ መሃል የኣንተ ጥያቄ ብቅ ኣለ።

ጫወታዉን ትተን በቁምነገር ሳስብ ኦሮሞን ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ የኢትዮጵያዊያን ሕዝብ ጥያቄ መልስ ማለት የምንችለዉ አስተዳደሮቻችንን መስርተን ኣስተዳዳሪዎቻችንን ሾመናል ማለት ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

እነ ሆረስም መርካቶ ዉስጥ ከታች እስከላይ መቸብቸብ ከቻልን፣ ከሰሜን እስክ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ዞረን መስራት ከቻልን፣ በዓመት ኣንዴ መስቃን ብቅ ብለን መስቀልን ካከበርን፣ መስቃን ላይ ሆረስ ተሾመ፣ ግዛቸዉ ተሹሞ ተላከ ምን ኣነጫነጨን የሚሉ ከሆነም መብት ኣላቸዉ።

ሆረስ፥

እኔ ደግሞ ልጅ ሆኜ የሰማሁኝ ቀልድ ብዙ ጉራጌዎች ከአማራ በላይ አማራ ነን ይላሉ የሚል ነበር።

ጀነተ ወይም ገነት ይመቻቸዉ እና (መቼም የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ሆነዉ ሌላ ቦታ ኣይሆኑም) በቅርቡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን የገሰጸዉን ኣንብቤ ያ የልጅነት ግዜ ቀልድ ኣስቆኛል።

እስቲ እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በሌላ የኢትዮጵያ ፕሮፌሰር የተገሰጸ ኣንድ የኦሮሞ ፕሮፌሰር መጥቀስ ትችላለህ?

ካልቻልክ ኣንተ በልጅነህ የሰማሀዉ ቀልድ ነዉ ወይስ እኔ በልጅነቴ የሰማሁት ቀልድ ነዉ በኢትዮጵያ ፕሮፌሰር የበለጠ የተረጋገጠዉ?
Last edited by Naga Tuma on 29 Apr 2024, 15:19, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 31066
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Horus » 29 Apr 2024, 02:23

ናጋ ቱማ፣
ዉሸታም። ጉራጌ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ነው ። ካማራ ጋር አዲስ አበባ ቆርቁሮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የገነባ አልፋና ኦሜጋ ኢትዮጵያዊ ነው። ጉራጌ ከራሱና ኢትዮጵያዊነት ሌላ ምንምና ማንም መሆንን ፍጹም ፈልጎ አያውቅም ። ይህ ዉሸት ከሆነ በሞት ልቀጣ ! አንተ ግን ይህው ለ50 አመት ትሞታለህ ትባክናለህ! ምን መሆን እንደ ምትፈልግ ግን አንተ እራስህ አታውቀም ። አትዋሽ ! ስለዚህ መልስ! ኦሮሞ ምን መሆን የሚፈልገው? የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? መስሉ ምንም ነው!!! መልሱ ኢትዮጵያን ማወክና ማቃወስ ነው !!!

Abere
Senior Member
Posts: 11311
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Abere » 29 Apr 2024, 15:00

Naga Tuma,

ማንኛውም ቁልፍ ችግር በአንድ ቃል ወይም ዐረፍተ-ነገር ይገለጻል። 1 ሺ ገፅ ጽሑፍ ስለ አንድ ችግር ቢያትትም ችግሩ በደንብ ከታወቀ አንድ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል። በርካታ የኦሮሙማ አቀንቃኝ ተማርን ባዮች ስለ ኦሮሞ ጥያቄ ኢንሳይክሎፒዳ ያህል ይጽፋሉ ያወራሉ - ዶክትሬት ድርግሪ ጽፈውበታል። ግን በአህጽሮት የኦሮሞ ያልተፈታ ጥያቄ ምንድነው ብለህ ስትጠይቃቸው አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራዋል ብለው ያርፋሉ። ያ ሁሉ ዙሪያጥምጥም ይችን ለመናገር ነው። ትልቁ ጥያቄ ያ ስያሜ አማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ከነ አካቴው የለም። ታዳያ ኦሮሙማዎች መጣላት የፈለገ ሰው የፍዬል ሻኛ አቅርቡ አይነት ነገር ከየት መጣ ነው? የኦሮሞ ልዩ መብት ምንድን ነው።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5569
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Naga Tuma » 29 Apr 2024, 20:36

Horus wrote:
29 Apr 2024, 02:23
ናጋ ቱማ፣
ዉሸታም። ጉራጌ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ነው ። ካማራ ጋር አዲስ አበባ ቆርቁሮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የገነባ አልፋና ኦሜጋ ኢትዮጵያዊ ነው። ጉራጌ ከራሱና ኢትዮጵያዊነት ሌላ ምንምና ማንም መሆንን ፍጹም ፈልጎ አያውቅም ። ይህ ዉሸት ከሆነ በሞት ልቀጣ ! አንተ ግን ይህው ለ50 አመት ትሞታለህ ትባክናለህ! ምን መሆን እንደ ምትፈልግ ግን አንተ እራስህ አታውቀም ። አትዋሽ ! ስለዚህ መልስ! ኦሮሞ ምን መሆን የሚፈልገው? የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? መስሉ ምንም ነው!!! መልሱ ኢትዮጵያን ማወክና ማቃወስ ነው !!!
ጥያቄዬ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ ኣላልክም ሳይሆን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን ስለምን ገሰጸ ነዉ።

ለምንድነዉ ዲሞክራሲ ቅርብህ ይሁን ስትባል ልቀጣ ቅርብህ የሚሆነዉ? ዲሞክራሲ ዉስጥ ለዘላለም ኑር እንጂ።

እንኳን ኣንተ ኣብዮት ተብሎ መቅሰፍት ከሆነዉ የተረፍክ ይቅር እና የኣጼዉ ፍሬዎች፣ መለስን ጨምሮ፣ ዲሞክራሲ ዉስጥ በተነሱ እላለሁ። ዲሞክራሲ ሜዳዉ ሰፊ ነዉ።

የሰለቸኝ ስህተቶችህን እያነበብኩ ጥቢ ጥቢ ማለት ነዉ።

የሰለቸኝ ኣንተም፣ ወንድምህም፣ ማዶ ለማዶ ቆማችሁ ኣዉቃለሁ ማለት እንጂ ይህን ኣዉቃለሁ፣ ያንን ኣላዉቅም ማለት ኣለመቻላችሁ ነዉ።

ኣሁን ደግሞ ጉራጌ ከኦሮሞ በላይ የሃገር ቆርቃሪነት ተሳታፊ ነበር እያልክ ነዉ?

የጉራጌ ራስ ጎበና ማን ነበሩ?

ኣንተም ፋሽን ነዉ ብለህ ጉራጌ ጀርባ ከመወሸቅ ወጥተህ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በሚዛናዊነት ማየት ትችላለህ?

ስትችል መግባባት ስለምያስችል ጥልቅ የሃገር ባህል ተመከር።

በሚከተሉት ሁለት ዐረፍተነገሮች መካካል ምን ልዩነት ኣለ?

ሆረስ ጎበዝ ቢሆንም ኣልፎ ኣልፎ ይሳሳታል።
ሆረስ ኣልፎ ኣልፎ ቢሳሳትም ጎበዝ ነዉ።

በባህል እላ ፊ እላሜ የሚባል የመግባብያ ጥበብ ኣለ።

በእንግሊዘኛም ጠቃሚ ጥበብ ነዉ ብለዉ እንደምያስተምሩት ኣዉቃለሁ። በኣጭሩም ፕሮኣክቲቭ ይሉታል።

ለመግባባት እንድያስችልህ ከእዉነት ጀምረህ፣ ስህተት ካለ ኣመልክተህ፣ እንዲታረም ኣስተያያት ከሰጠህ ተመስገን ትባላለህ። መግባባት ቻልክ ማለት ነዉ።

ያለዝያ ዝም ብለህ ዘለህ ዉሸታም ስትል ባህል እንደሌለዉ ዉፍ ዉፍ ኣልክ ይባላል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5569
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Naga Tuma » 29 Apr 2024, 23:11

Abere wrote:
29 Apr 2024, 15:00
Naga Tuma,

ማንኛውም ቁልፍ ችግር በአንድ ቃል ወይም ዐረፍተ-ነገር ይገለጻል። 1 ሺ ገፅ ጽሑፍ ስለ አንድ ችግር ቢያትትም ችግሩ በደንብ ከታወቀ አንድ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ይገልጸዋል። በርካታ የኦሮሙማ አቀንቃኝ ተማርን ባዮች ስለ ኦሮሞ ጥያቄ ኢንሳይክሎፒዳ ያህል ይጽፋሉ ያወራሉ - ዶክትሬት ድርግሪ ጽፈውበታል። ግን በአህጽሮት የኦሮሞ ያልተፈታ ጥያቄ ምንድነው ብለህ ስትጠይቃቸው አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራዋል ብለው ያርፋሉ። ያ ሁሉ ዙሪያጥምጥም ይችን ለመናገር ነው። ትልቁ ጥያቄ ያ ስያሜ አማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ከነ አካቴው የለም። ታዳያ ኦሮሙማዎች መጣላት የፈለገ ሰው የፍዬል ሻኛ አቅርቡ አይነት ነገር ከየት መጣ ነው? የኦሮሞ ልዩ መብት ምንድን ነው።
አበረ፥

የ50 ዓመታት ጥያቄ ያልከዉን በየምዕራፉ ብንከፋፍል የመጀመርያዉ ምዕራፍ የሚመስለኝን በኣንድ ህብራቃል ገለጽኩት እኮ፣ ለምሳሌ ያህል ቁምላቸዉ ብዬ።

የማገባደጃዉ ምዕራፍ ቁምላቸዉ ተሹሞ ከአዲስ አበባ የሚላክላችሁ ሳይሆን ቁምልንን ወክላችሁ ወደ አዲስ አበባ ትልካላችሁ ብለሃቸዋል? ካልካቸዉ ይህ ይቀራል ያሉህ ኣለ?

በዚህ 50 ዓመታት መካከል በመጀመርያዉ 17 ዓመታት ዉስጥ ተዓምራዊ በሚመስል ሁኔታ የነፃነት እና ለኣፍርካ ነፃነት ተምሳሌት የሆነች ሃገር ዉስጥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል የሚል ኣዙሪት ነገሠ።

በተቀሩት 33 ዓመታት ዉስጥ ነዉ ሌላ ተዓምር በሚመስል ሁኔታ ኣዙሪቱ ተደፍቶ የሃገር ሉዓላዊነት የቀና የሚመስለዉ።

ኣሁን እነዚህ ተዓምራት የሚመስሉ ሁኔታዎችን እያስታወስን ነዉ በኣብዛኛዉ በኣንድ ቋንቋ የምንወያየዉ።

እኔ ኦሮምኛንም ኣማርኛንም ኣእምሮዬ ነፃ ሆኖ እናገራለሁ፣ እጽፋለሁ። ለዚህ ኣእምሮዬ መቼ እና በምን ምክንያት ነፃ እንደሆነ በግልጽ ኣስታዉሳለሁ።

ኣንተም እንደ እኔ ሁለቱንም ቋንቋዎችን በነፃ መናገር እና መጻፍ ትችላለህ? ከቻልክ እሰየዉ ነዉ። ካልቻልክ ክርክሩን ለወኪሎቹ መተዉ ነዉ ተገቢ የሚሆነዉ። ወኪል ካልሆንክ ሃገር ማድረግ የምትችለዉ ቁምልኖች በተገቢ ሁኔታ እንዲወከሉ ማድረግ ነዉ። ኣይዴለም?

Tiago
Member
Posts: 2071
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Tiago » 30 Apr 2024, 01:33

Gaal comes from Galla which was used for the Oromos and since they were foreign to somalis it came to mean foreigner and used for everyone. Gaalo originally meant non Somali, it was a word used in the pre Islamic era, for anyone that was NOT somali. Habashi, oromo etc were all called "Gaalo"
the word 'galla' is not amharic by origin despite the childish tantrum we hear from bigoted oromos.

Horus
Senior Member+
Posts: 31066
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Horus » 30 Apr 2024, 02:01

Naga

አንተ የሌለህን ታሪክ፣ ማናነትና፣ ሚና ለመፈብረክ ለምትዘረግፈው የቃላቶች ድሪቶ መልስ ምስጠት አይደለም፣ አንብቤውም አላቅም። አንድ ነገር ላንዴም ለሁሌም ተገንዘብ። ጉራጌን በዚያ በጭለማው ዘመን እንደነ ጋፋት፣ እንደነ ዛይ፣ እንደነ ባሊ ዘሩን ማጥፋት ያልቻልክ ዛሬ ባትሞክረው ይሻላል ። እድሜ ለጄኔቲክ ሳይንስ በቅርቡ ማን የማን ዝርያ እንደ ሆነ የማይዋሸው ባዮሎጂ ያሳየናል ። ተረት እንደ ታሪክ የሚዘራበት ዘመን ተዘግቷል። እስከዚያ ታገስ!

አበረ የጠየቀህን እጅግ ቀላል ጥያቄ መልስ? ኦሮሞ ምንድን ነው የሚፈልገው? በቃ!

እኔ ለምንድን ነው የኦሮሞ ፖሊሶች ያገር አርማ ለብሰው የዘረፋና ገዳይ ቦድን የሚሆኑት? ብዬ አልጠይቅህም!!! ግን ካልቸርህ አንድ ግዙፍ በሽታ እንዳለው ይነግረኛል! ለምንድን ነው ኦሮሞ በቡድን በቡድን ሆኖ ቄስና መነኩሴ የሚያርደው? ብዬ አልጠይቅህም! ግን ካልቸርህ አንድ ግዙፍ በግፍና ደም የላሸቀ በሽታ እንዳለው ይነግረኛል!

እናም ሁለተኛ ከኔ ጋር ስለ ዘመነ አመክንዮ እያነሳህ አታስመስል !! መጀመሪያ አንተና ያንተ ነፍስ የተሰራችበት ካልቸር ከዘመነ አረመኔነት ለምን መላቀቅ እንዳቃተህ ሜዲቴት አድርግ! ያ የሚያስከብርህ ይሆናል!!

Selam/
Senior Member
Posts: 11981
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: DDT የኦሮሞ ጥያቄ ምንድን ነው? ተምሬያለሁ አክራሪ ኦሮሞ ብዙ ካወራኝ በኋላ መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ጥያቄ አማራ ኦሮሞን *** ብሎ ይጠራል ብሎኝ አረፈ።አማርኛ ውስጥ ግን ይህ ቃል የለ

Post by Selam/ » 30 Apr 2024, 05:16

’የኦሮሞ ህዝብ’ ከማለት ‘አብዛኛው የኦሮሞ ምሁራን‘ ማለትን እመርጣለሁ ምክንያቱም የውሸት ትርክትን፣ የቃላት ስንጠቃንና ጥላቻን አቡክተው የሚጋግሩት እነሱ ተማርን ነን ባዮቹ ስለሆኑ። ህዝቡ በፖለቲካ አቀንቃኞቹ ትርክት የሚነዳ ጀሌ ነው ስለዚህ ጀሌ ላይ ጉልበትን ማባከን መክሸፍ ነው።

አበረ እንዳለው፣ የኦሮሞ ምሁራን ጥያቄ ቅርፅና ይዘት የሌለው የማይጨበጥ ጉም ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ወያኔና ሻቢያ ባዘጋጁላቸው ሸምቀቆ ገብተው፣ አፄ ቴዎድሮስን ያስገደለውን የሉድዊሽ ክራፍ አፈ ታሪክ ሸምድደው፣ ‘ከኢትዮጵያ መንገጠል ነው የምንፈልገው’ ሲሉ ነበር። ወያኔ እግሯ ሲቀጥንባት፣ ስልጣኑን ለነሱ አስረክባ ወደ መቀሌ ስትኮበልል ደግሞ መገንጠል የሚለውን ቃል እኛ ኦሮሞዎች አንስተነው አናውቅም በማለት እራሳቸውን ካዱ። የሚገርመው፣ ስልጣንም ከያዙና ህዝቡ ሆ ብሎ ሹመታቸን ካጸደገላቸው በኋላም፣ ሃገር መምራት አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከአኩራፊነት ወደ ፍፁም አራዊትነትና አውሬነት መለወጣቸው ነው።

ስለዚህ የኦሮሞ ኢሊቶች መሰረታዊ ችግራቸው እንደ ጥላ እየተከተለ የሚያሳድዳቸው ‘የአናሳነት ስሜታቸው’ ብቻ ነው። እጃቸው ላይ ባሉት ትልልቅ እሴቶቻቸው ብቻ ረክተው መኖር አይችሉም ፤ ከሌሎች ህዝቦችም ጋር በተመዛዘነና በተቀናጀ ሁኔታ ተባብረው መኖርም አይችሉም። ምክንያቱም ሁሌም አጠገባቸው ያለው ሌላ ሰው ወይንም ህዝብ በሁሉም መመዘኛ የሚበልጣቸውና የሚንቃቸው ስለሚመስላቸው ነው።

እነዚህ የአናሳነት ባህርይ መገለጫዎች ናቸው ዛሬ የብልፅግናን የአስተዳደር አቅጣጫ በሰመመን የሚዘውሩት። መሰረታዊ ሳይኮሎጂን ያጠና ሰው ደግሞ እንደሚገነዘበው፣ የአናሳነት ባህርይ ያለበት ሰው፣ ሃገር አይደለም የራሱን ህይወት በትክክል መምራት አይችልም። ስለዚህ ዓብይ ሺህ የካድሬ መአት ቢደረደርና፣ ጀሌ ቢያሰለጥን በትንሽነት ስሜት የተንሰራፋው ውጥንቅጥና አፀያፊ አስተዳደሩ እንደ እንቧይ ካብ መናዱ አይቀርም።

“ይህን ሁሉ ታያላችሁ፧ እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተክቦ የምታዩት፣ ሳይፈርስ እንዲሁ እንዳለ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ አይኖርም” ማቴዎስ ፳፥፪፬

Post Reply